Web Content Display Web Content Display
Minimize Maximize

Interview Interview
Minimize Maximize

 የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የከተማ ልማት ዘርፍ ኃላፊ

 ከሆኑት ከክቡር አቶ ኤቢሣ ዲንቃ

ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ

1. የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ሴክተር የእድገትና ትራንሰፎርሜሽን እቅድ ከግብ ለማድረስ ከአደረጃጀቱና አሰራሩ አንፃር እስከ አሁን ያከናወናቸዉን ሥራዎች ቢገልፁልን፡፡


የኦሮሚያ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ በስሩ የሚገኙትን ሴክተሮች በክልል፣ በዞንና በከተሞች ተደራጅተው ወደ ሥራ ገብተዉ ለውጦች እያስመዘገቡ ሲሆን በተሟላ መልኩ ወደ ሥራ ለመግባት ግን ይህ አደረጃጀት ከተሞች ካላቸዉ ተልዕኮ አንፃር ስንመለከት የተሟላ አደረጃጀት ነው ብሎ መውስድ ያስቸግራል፡፡የሚቀሩት ብዙ ነገሮች አሉ ማለት፡፡እነዚህ አደረጃጀቶች አሁን አለም ከደረሰበት እና የአለም ከተሞች ከደረሱበት ደረጃና ከህብረተሰቡ ጥያቄና ፍላጎት አንፃር ሲታይ ተልዕኮዉን ከግብ ለማድረስ አሁን ካለበት አደረጃጀት በብዙ መደራጀት መጠንከር ይኖርበታል፡፡


በተለይም የትራንስፎርሜሽኑን ዕቅድ ከማሳካት አኳያ የመጀመሪያ የትራንስፎርሜሽኑን ዕቅድ ወደ መጠናቀቅ እየሄደ በመሆኑ የሚቀጥለው የትራነስፎርሜሽን ዕቅድ ይኖረናል ያሄንን ዕቅድ ጭምር ሊሽከም የሚችል አደረጃጀት ለመፍጠር ከክልል እስከ ከተማ ቀበሌ ድረስ የአደረጃጀት ሥራዎችን በመፈተሽ መስተካከል ያለባቸውን ነገሮች ለማስተካከል ዝግጅቶች እየተደረጉ ናቸው፡፡ ለዚህም ጥናቶች ተካሄደዉ ወደ መጠናቀቅ እየተደረሰ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜም ጥናቱ ሲጠናቀቅ ወደ ሥራ የሚገባ ይሆናል፡፡ ይህ አደረጃጀትና አሰራር ቀሪውን የትራንስፎርሜሽን እቅድ ከግብ ለማድርስ ከፍተኛ አስተዋፆ ሊያበረክት ይችላል፡፡ በዋናነት ደግሞ የዘንድሮ ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ሰራዎቻችንን ከማስካት አኳያ ከፍተኛ ሚና ስለሚኖረው ይህንን ቶሎ አጠናቆ ወደ ሥራ መግባትና የተሟላ ሥራ ለመሰራት የያዝናቸውን ሥራዎች በተለይም ሀገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ ብሎም ከዛ በላይ የበለፀገች አገር ለመፈጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ዕገዛ ይኖረዋል፡፡

እሰካሁን ድረስ በዚህ መልኩ ባለዉ አሰራርና አደረጃጀት በረካታ ርቀት ሄደናል ይህ አሰራር እና አደረጃጀት ደግሞ ለሥራችን አስፈላጊ እስከ ሆነ ድረስ በየጊዜዉ እየታየና እየተፈተሸ መሄድ ይኖርበታል፡፡ ዋንኛዉ ግን አደራጃጀት ብቻውን ሥራ ይሰራል ማለት አይደለም፡፡ የመጀመሪያው ሥራ በሰው አመለካከት ላይ የሚሠራ ነው፡፡ የአመለካከት ለውጥ የማምጣት ጉዳይ ለሁሉም ሥራዎች ወሣኝና ቁልፍ ሚና አለዉ፡፡ አሁን ባለው አደረጃጀትና አስራርም ከዚህ በላይ መስራት ይቻል ነበር፤ በተፈለገዉ ደረጃ የልተሰራበት ምክንያት በአንድ አንድ ቦታዎች ላይ የሚታይ ክፍተቶችና ድክመቶች በዋነኝነት ከአመለካከት ጋር የተያያዙ ችግሮች በመሆናቸዉ ነዉ፡፡

የሰው ልጅ ሥራዎቹን ከማከናወኑ በፊት ቅድምያ ሊሰጠዉ የሚገባዉ ጉዳይ በስራዉ ላይ ያለዉ አመለካከት ከከፍተኛ ደረጃ የማድረስ ጉዳይ ነዉ፡፡ አመለካከቱ ላይ የተሟላ ነገር ካለና በትክክለኛ የአመለካከት መስመር ውስጥ ከገባ ቀሪው የአደረጃጀትና የአሰራር ሂደቶች ለዚህ አጋዥ ናቸው፡፡ ይህን ለማድረግ በርካታ የአመለካከት ለውጥ ሥራዎች በአመራሩና በህብረተሰቡ በሠፊዉ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የሚፈለገዉን የአመለካከት ደረጃ ላይ እስክንደርስ ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በሚቀጥሉት ግዜያትም በዚህ ረገድ ሰፊ ስራ ይጠብቀናል ማለት ነዉ፡፡

Pages: 1  2  3  4  5