1.አፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
ሴክተር መ/ቤቱ በቢሮ ኃላፊና በ2 ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሚመራ ሲሆን በዋናነት የገጠር መንገድ ባለስልጣንን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲን የከተሞች አስተዳደርና የማዘጋጃ ቤቶችን በስሩ ተጠሪ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ሴክተር ነዉ፡፡
2.ተልዕኮ
የተቋሙን ተገልጋዩችና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበርና በማቀናጀት ደረጃዉን የጠበቀ አገልግሎት በከተሞች እንዲቀርብ በማድረግ ከተሞችን የልማት ማዕከላት እንዲሆኑና ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መገንባት
3.ራዕይ
ለኑሮ ምቹና ተወዳዳሪ የሆኑ ከተሞች እና አገር አቀፍ ደረጃዉን የጠበቀ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተፈጥሮ ማየት
4.እሴቶች
ሴክተር መ/ቤቱ ያስቀመጠዉን ራዕይ ተልዕኮና ዓላማ ለማሳካት እንዲሁም በተሰጠዉ ስልጣንና ተግባር መሰረት ሃላፊነቱን ለመወጣት የሚከተሉትን መሰረታዊ እሴቶች አስቀምጧል፡፡
1.ከተሞችን ልማትና የመልካም አስተዳደርን ማረጋገጥ
2.የከተማና የገጠር ትስስርን ማጠናከር
3.የሀገሪቱን የህንፃ ኮድ ማስከበር
4.የከተሞችን ዕድገት ፕላን በትክክል እንዲተገብሩ ማድረግ
5.በአዋጅ የተሰጠ ስልጣንና ተግባር
የአፋ/ብ/ክ/መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 55/2003 አንቀፅ መሰረት የልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የሚከተሉትን ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፡፡
v የከተማ የአከታተምን በሚመለከት ጥናት ያካሂዳል የከተማን መመዘኛ ያወጣል
v ከተሞች የአካባቢያቸው የልማት ማዕከል እንዲሆን ሁለገብና ተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል
v የከተሞችን አቅም ለማሳደግ የሚያስችል የአመራርና የአደረጃጀት ስርዓት ይቀይሳል
v በከተሞች ለኢንቨስትመንት ለማህበራዊ አገልግሎት ለመኖሪያ ቤት ስራ የሚሆን መሬት ያዘጋጃል ያድላል ይቆጣጠራል
v በከተሞች ማዘጋጃ ቤት እንዲያቋቁሙ እዉቅና ይሰጣል
v የቅየሳ ስራዎች ያካሂዳል መሰረታዊ የከተማ ልማት ፕላን ያዘጋጃል
v የከተሞች ፅዳትና ዉበት ለመጠበቅ የሚያስችል የአሰራር መመሪያ ማንዋሎች መመዘኛ ያወጣል ተግባራዊነቱን ይከታተላል
v በክልል መንግስት ባለቤትነት የሚገኙ ቤቶችን ያስተዳድራል
v በክልል ከተሞች ዉስጥ የመኖሪያ ቤት ችግሮችን ለማቃለል የቁጠባ ቤቶች እንዲሰሩና እንዲከራዩ ሁኔታዎችን ይመቻቻል ያበረታታል የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል
v በክልሉ መንግስት በጀት በሚሰሩ ህንፃዎች ዲዛይኖችና የግንባታ ዉሎች እንዲዘጋጁ በማድረግና የግንባታ ስራዎች በመቆጣጠር ረገድ አስፈላጊዉን ድጋፍ ይሰጣል
v መሀንዲሶችንና አርክቴክቶችን ይመዘግባል የሙያ ችሎታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል የስራ ተቋራጮችንና የአማካሪዎችን ደረጃ ይወስናል
v በክልሉ የሚሰሩ የኮንስትራክሽን ስራዎች ይቆጣጠራል
በፌደራልና በክልል ደረጃ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን በሚመለከት ወጥ የደረጃ መመዘኛ መመሪያዎችን በክልሉ መተግበሩን ያረጋግጣል
በክልሉ የሚሰሩ ህንጻ መንገድና ሌሎች ሲቪል ስራ ዲዛይን ግንባታ ደረጃዉን የጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል
በክልሉ መንግስት በጀት የሚሰሩ የመንግስት ኮንስትራክሽኖች በተገባላቸዉ ዉል መሰረት የጥራት ደረጃቸዉን የጊዜና የዋጋ ገደቦች ተጠብቀዉ መሰራታቸዉን ይቆጣጠራል
በክልሉ ዉስጥ የሚገኙትን ከተሞች ዕድገት በጊዜዉ እያጠና ደረጃ ሽግግር እንዲደረግላቸዉ ሃሳብ ያቀርባል ማእከላትን እንዲሆኑ ሁለገብና የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል የከተማ አስፋልትና የእድገት አቅጣጫዉን ያጠናል ይከታተላል በክልሎች ዉስጥ መሪ ፕላኑን የጠበቁ የመሰረተ ልማ ት ስራዎች የሚስፋፉበትን ዘዴ ይቀይሳል ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል
በክልሉ ዉስጥ የሚገኙ 5 ከተማ አስተዳደሮችን በእቅድና የከተማ ፕላን አዘገጃጀትና አፈጻጻ በሰዉ ሃይል አስተጋገርና ስምሪት ረገድ የከታተላል የቴክኒክና የሙያ ድጋፍ ይሰጣል ጥያቄ ሲቀርብለትም የገጠር ቀበሌ ማእከላትና የከተሞች ፕላን ይሰራል ስራዉን በበላይነት ይመራል
ከተሞች ሁሉን አቀፍ በሆነ ደረጃ ሊከተላቻዉ የሚገባቸዉ ልዩ ልዩ የህንፃ ማእቀፎች እንዲኖሩ ያደርጋል እድገታቸዉን ተከትሎ ያሻሽላል
ከተማ መሬት ወጭ ቆጣቢና ዉ ታማ በሆነ አግባብ አቅም ላይ እንዲዉል የአሰራር ስርኣቶችን ይዘረጋል አፈጻጸማቸዉን ይከታተላል ይቆጣጠራል
3. አደረጃጀት
ከተማ ልማትነ ኮንስትራክነቨን ቢሮ ሚከተሉትን አራት ዋና እና ስድስት ደጋፊ የስራ ሂደቶች ያጠቃልላል
Ø የዲ/ግን/አስ/ዋ/የስራ ሂደት
Ø የከ/ፕ/ጽ/ዉበ/ዋ/የስራ ሂደት
Ø የከ/መ/ል/የይ/አስ/ዋ/የስራ ሂደት
Ø መል/አስ/ዋ/የስራ ሂደት
Ø የጥ/ዕ/በጀ/ዝ/ደጋፊ የስራ ሂደት
Ø የግ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት
Ø የሰ/ሀ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት
Ø የኦ/ ደጋፊ የስራ ሂደት
Ø የኢ/ቴ/ደጋፊ የስራ ሂደት
Ø የመ/ሴ/ህ/ግን/ደጋፊ የስራ ሂደትን ጨምሮ በአጠቃላይ 182 ሰራተኞችን በዉስጡ የያዘና የራሱ የሆነ ራእይ ተልእኮ ስልጣንና ተግባር እሴቶች እንዲሁም የትኩረት አቅጣጫዎችና የትኩረት መስኮች እንዲኖሩትና በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ሰፊ የሆነ ክልላዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ተደርጎ አደረጃጀቱ እስከ ከተሞች ማ/ቤቶች ከተማ አስተዳደሮች ደረጃ ድረስ የተቃቃመ ሴክተር ነዉ