Web Content Display Web Content Display
Minimize Maximize

የከተማልማትናኮንስትራክሽን  ቢሮ በ1985 ዓ.ም የስራና ከተማ ልማት ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በሚል ስያሜ ተዋቅሮ እስከ 1993 ዓ.ም ድረስ ገጠር መንገድ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ስራዎችን ጨምሮ እንደ አንድ የስራ ዘርፍ በመውሰድ ሲንቀሳቀስ ነበር፡፡ ከዚያም የክልሉ መንግስት በ1993 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ የክልሉን አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመደንገግ ባወጣው አዋጅ ቁጥር 15/1994 ዓ.ም መሠረት የስራና ከተማ ልማት ቢሮ በሚል ስያሜ እንደ አንድ አስፈጻሚ መስሪያ ቤት በመሆን ተቋቁሟል፡፡ ቢሮው የተቋቋመበት ዋነኛው ምክንያት ወይም ዓላማ በክልሉ በሚገኙ አጠቃላይ ከተማ ነክ ጉዳዮች በመሳተፍ በከተሞች መልካም አስተዳደርን መሠረት ያደረገ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግና በከተሞች ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ስራ አጥነት በመቀነስ ሠፊ የስራ ዕድል በመፍጠር የስራ አጡን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ነው፡
ቢሮው እንደገና በ2003 ዓ.ም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር በተደረገ ሀገራዊ የአደረጃጀት ለውጥ ምክንያት የክልሉ አስፈጻሚ አካላትም ይህንን የአደረጃጀት ለውጥ በመቀበል ቢሮው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በሚል ስያሜ በአዋጅ ቁጥር 55/2003 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን ቢሮው የራሱ የሆኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ስልጣንና ተግባር፣ እሴቶች እንዲሁም የትኩረት አቅጣጫና የትኩረት መስኮች እንዲኖሩትና በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፉ ሠፊ የሆነ ክልላዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ታስቦ የተቋቋመ ክልላዊ ቢሮነው፡፡    

ሴክተር/ቤቱበቢሮ ሃላፊናበምክትል ቢሮ ሃላፊየሚመራ ሲሆን በዋናነት የገጠር መንገድ ባለስልጣንን፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲን፣ የከተሞች አስተዳደርንና የማዘጋጃ ቤቶችን በስሩ ተጠሪ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ሴክተር ሲሆን አደረጃጀቱም በሶስት ዋና ዋና እና ስድስት ደጋፊ የስራ ሂደቶችን ያጠቃልላል እነዚሀም የዲዛይን፣ ግንባታና አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት,የከተማ ፕላን ጽዳትና ውበት ዋና የስራ ሂደት, የከተማ መሬት ልማትና የይዞታ አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት, የጥናት፣ ዕቅድና በጀት ዝግጅት ደጋፊ የስራ ሂደት, የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት, የሠው ሀብት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት, የኦዲት ደጋፊ የስራ ሂደት, የአይ. ሲ.ቲ ደጋፊ የስራ ሂደት, የመንግስት ሴክተር ህዝብ ግንኙነትን ጨምሮ በአጠቃላይ 170 ሠራተኞችን በውስጡ የያዘና የራሱ የሆነ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ስልጣንና ተግባር፣ እሴቶች እንዲሁም የትኩረት አቅጣጫዎችና የትኩረትመስኮች እንዲኖሩትና በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፉ ሠፊ የሆነ ክልላዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ተደርጎ አደረጃጀቱ አስከ ከተሞች/ማ/ቤቶች/ከተማ አስተዳደሮች ደረጃ ድረስ የተቋቋመ ቢሮ ነው፡፡