ቀን 15/04/2012
ሰሞናዊ ዜና
በከተማ ልማት ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድርክ ተዘጋጀ።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በጋራ በመሆን በከተማ ልማት ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች ላይ በክልሉ ላሉ ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ክቡር አቶ ሀሩን ዑመር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስልጠናውን አዘጋጅቶ ለክልላችን አመራሮችና ባለሙያዎች ለመስጠት በመምጣታቸው አመስግነው ስልጠናው በዘርፉ ፖሊስዎች ስትራተጅዎች የህግ ማዕቀፎችና አሰራሮች በቂ ግንዛቤ ያለው የከተማ አመራር በማብቃት በከተሞች የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ሊያፋጥንል የሚችል አንድ እድል ነው ብለዋል።
አክለውም የኢፊዲሪ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለዚህ ዘርፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ታሳቢ በማድርግ የክልላችን የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በብቃት ዘርፉን እንዲመሩና ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድርግ የሚያስችልና በአመራሮችና በባለሙያዎች የሚታየውን የኪራይ ሰብሳብነትና ህዝብን የማገልገል የአስተሳሰብ ዝንፈቶችን የሚቀርፍና ዲሞክራስያዊ የህዝብ አያያዝና ልማት ተሳትፎን ከማሳደግና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማትን ለማስፋፋት የሚረዳ ትልቅ ስልጠና እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የከተማ ልማትና፣ ቤቶች ዘርፍ ሚኒስቴር ዴእታ የሆኑት አቶ መስፍን አሰፋ መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ ስልጠናው በከተማ ልማት ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን በመግለጽ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቂ ግንዛቤና ዕውቀት ኑሯቸው ከተማቸውን በአግባብ እንዲመሩና ለህብረተሰቡ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስልጠና መሆኑንን እንዲሁም አሁን አገራችን እየተመራችበት ያለውን ኢንዱስትሪ መር የዕድገት አቅጣጫን በመከተል ላይ የምትገኝ መሆኗን በመግለጽ ሰልጣኞች ይህን አጋጣሚ እንደመልካም ዕድል በመቁጠር በትጋት ስልጠናውን በመውሰድ ወደተግባር እንዲለውጡ አሳስበዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም በፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ እንዲህ ዓይነት ስልጠና መሰጠቱ ለስራቸው አስፈላጊና የሚጠቅም መሆኑን ገልጸው በቀጣይም የዚህ አይነት ስለጠናዎች ተጠናክረው ቢቀጥሉ ስራችንን የተቃና ያደርግልናል በማለት ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ስልጠናው ከታህሳስ 13-25 /2012 ዓ/ም የሚቀጥልና የሚቀርቡ ሰነዶች በዕጃችው የሚደርስ ስለሆነ ከስልጠናው በተጨማሪ ወደስራ ስትገቡ ሰነዱን እያነበባችሁ ያለባችሁን ክፍተት በመሙላት የሚሰራ እንደሆነ ታሳቢ እንዲደረግ ስልጠናውን የሚሰጡ አሰልጣኞች አስረድተዋል። ይህን በማድረግ ስልጠናው በሰንድ ይቀርብና የበለጠ ለማስረጽ እንዲቻል በቡድን ሆነው በውይይት የሚያዳብሩበት ሁኔታ በመፍጠር ስልጠናው እየተሰጠ የሚገኝ መሆኑን የዘገበው የቢሮው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ክፍል ነው።