
የካቲት 28, 2025
(ሆሳዕና፣የካቲት 16/2017) በኢፌድሪ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር በወ /ሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልኡክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል
የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ /ሮ ጫልቱ ሳኒ በጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ውጤታማ ናቸው ብለዋል።
በክልሉ በመንግስት እና በግል የኢንቬስትመንት ልማት ስራዎች ላይ የታየው አበረታች ውጤት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
ለኢትዮጵያ ከተሞች የትንሳኤ ዘመን ነው ያሉት ሚኒስትሯ ከተሞቻችን አምራች፣የፈጠራ ማዕከል እንዲሁም የብልጽግና ማሳያ እንዲሆኑ የተጀመረው ጥረት ውጤታማ ስለመሆኑም አመላክተዋል ።
ለረጅም አመታት ግንባታቸው ሲጓተት የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማስቀጠል የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሯ በአብነት ጠቅሰዋል።
በከተሞች የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ለማዘመን የተጀመሩ ስራዎች መሻሻል ማሳየታቸውንም ጠቅሰዋል።
የመንገድ መሠረተ ልማት ስራ ማስፋፋት፣ ጽዱ ከተማ እና አረንጓዴ ልማት ስራን ማጠናከር እንደሚገባም አስረድተዋል።
በከተሞች የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት፣የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ተዛማጅ የከተማ ልማት ስራ ላይ የተጀመሩ ተግባራትን ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባም ሚኒስትሯ አብራርተዋል።ማ/ኢ/ክ/ኮሙዩኒኬሽን