አዲስ አበባ፣ ህዳር 30/2017 ዓ.ም፡- (ከ.መ.ል.ሚ) ሀገራዊ የመንገድ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ማጠናቀቅ እንዲቻል በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ የትምጌታ አስራት ገለፀዋል፡፡
በዓለም ባንክ፣ በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ አበዳሪና ድጋፍ ሰጭ የፋይናንስ ተቋማት አማካኝነት ለሀገራዊ የመንገድ ፕሮጅክቶች የሚመደብ በጅትን ተግባራዊ ለማድረግ ከፌደራል እስከታችኛው የሚገኝ የመንግስት መዋቅር እንዲሁም ወሳኝ የሚባሉት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን መወጣት በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት ተካሂዷል ።
ሚኒስትር ዲኤታው አቶ የትምገታ አስራት ለፕሮጅክቶቹ መጓተት ብሎም እስከመቋረጥ የሚያደርሱ ምክንያቶችን ብለው ያነሷቸው ሀገራዊ የጸጥታ ችግር፣ የካሳ ክፍያ፣ ወቅታዊ የዶላር ምንዛሬ በየወቅቱ እያሻቀበ መሄዱ፣ የግብዓት አቅርቦቶ በተለይ ሲሚንቶ፣ ነዳጅ፣ የመሳሰሉት ከፍተኛ ማነቆዎች መሆናቸውን ገልጸዋል ፡፡
ታዲያ እነዚህን ተግዳሮቶች ጊዜ ሳይሰጣቸው በወቅቱ ለመፍ