ህዳር 18, 2025

ሰመራ ሎጊያ ፤ ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ)

በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክብር አቶ አወል አርባ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

የመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ህብረተሰቡ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም አገልግሎቶችን በቀላሉ በአንድ ቦታ የሚያገኝበት ማእከል ነው።

በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ ተመርቆ አገልገሎት ሲጀምር ዜጎችን የሚገባቸውን ክብር በመስጠት ዘመኑ የደረሰበትን ቴክናሎጂ ተጠቅሞ ህዝቡ እፎይ ብሎ አገልግሎት የሚያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር)በበኩላቸው መሶብ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ በአንድ ማዕከል በክብር እና በቅልጥፍና አገልግሎት የሚሰጥበት ሲሆን ይህ የመሶብ ምርቃት አንዱ የኢትዮጵያ ማንሰራራት መገለጫ ነው ብለዋል።

ክቡር አቶ አወል አርባ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ለአንድ ማዕከሉ እዚህ መድረስ ከፍተኛ አሰተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅናና ሽልማት በመስጠት የዕለቱን ፕሮግራም ተጠናቋል።

Posted in: ዜና