ህዳር 20, 2025

ሠመራ፤ ሕዳር 09፣ 2018 ዓ.ም (ከመልሚ)

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ሰመራ ገብተዋል።

ምከትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ሰመራ ‘ሱልጣን አሊሚራህ ሃንፈሬ’ አየር ማረፊያም ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል አርባ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና የክልልና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍል ተወካዮቾ ደማቅ አቀባባል አድርገውላቸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰመራ በሚኖራቸው ቆይታም ላለፉት ተከታታይ ቀናት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ በነገው እለት እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀውን 10ኛው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ማጠቃለያ መርሃ-ግብርን እንደሚታደሙም ይጠበቃል።

ለ10ኛ ግዜ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተከበረ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ላላፉት ተከታይይ ቀናት በባዛርና ሲምፖዚየምን ጨምሮ በተለያዩ ኩነቶች ሲካሄድ ቆይቶ ነገ ፍጻሜውን ያገኛል።
በፍረሙ የተሻለ ስኬታማ ስራ የሰሩና እራሳቸውን በአግባቡ ያስተዋወቁ ከተሞች ይሸለማሉ ቀጣይ 11ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አዘጋጅ ከተማ ይፋ ይደረጋል ።

Posted in: ዜና