ህዳር 12, 2025

ቢሾፍቱ፣ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) አቶ ብርሃኑ ይሄንን ያሉት የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ ፕሮጀክት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ከፌዴራል እና ከክልል የዘርፉ አመራሮች እንዲሁም የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ከተሞች በተገኙበት በቢሾፍቱ ከተማ በተደረገ የግምገማ መድረክ ላይ ነው።

ፕሮጀክቱ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ የሩሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ከመቀየር ባለፈ ጠዋሪ ቀባሪ የሌላቸው አረጋዊያን የሚረዳ፣ የዜጎችን የስራ እድል የሚፈጥር፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያረጋግጥ፣ መሆኑንም አልጸዋል አቶ ብርሃኑ።

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የከተማ ገጽታን የሚያሻሽል እና የአረንጓዴ ልማት እና የደረቅ ቆሻሻ አያያዝን በማሻሻል ረገድ ጠቀሜታዎች ያሉት እንደሆነና የተመለመሉ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች የስልጠናና ድጋፍ እንዲሁም ክትትል እንደሚያደርግ ሀላፊው አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

Posted in: ዜና