ህዳር 17, 2025

ሰመራ ሎጊያ፣ ህዳር 6/2018 ዓ.ም፣ (ከመልሚ)

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዛሬው ዕለት በይፋ የተጀመረውን 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ተከትሎ በተጓዳኝ ከሚካሄዱ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነው የፓናል ውይይት መድረክ መካሄድ ጀመረ።

የመጀመሪያው የፓናል ውይይት የኢትዮጵያ የክትመት ታሪክ አመጣጥ ፣ በሂደት የገጠሙ ችግሮች እና ለዘላቂ ልማት ያሉ ዕድሎች በመደመር መንግስት የሚል ስነድ በዶ/ ር አማን አሰፋ፣ በከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ሥራ አስፈጻሚ ቀርቧል።

እንደ ዶ/ር አማን ገለጻ በመደመር መንግስት ከተሞች ሲመሰረቱ የአስተሳሰብ እና የአመለካከት ለውጥ ያለው የአመራር ሞዴል መከተል እንደሚያስፈልግ ገልጸው ሁሉ-አቀፍና አሳታፊ የሆነ በፕላን የሚመራ ከተማን መገንባት የመደመር መንግስት እሳቤ እንደሆነ ገልጸው በፕላን የሚመሩ የዘመኑ ከተሞችን በመገንባት ከተሞችን የብልጽግና መዳረሻ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የቀረበውን የውይይት ሠነድ መነሻ በማድረግ ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዲብራሩ ለፓናሊስቶች ባቀረቧቸው ዋና ዋና የፖሊሲ አቅጣጫዎች ላይ እና ከተወያዮች ለተነሱ ጥያቄዎች በመ ድረኩ ላይ በተሰየሙ ፓናሊስቶች አማካኝነት የተብራራ መረጃ ተስጥቶባቸዋል።

በመጨረሻ ክብርት ሚኒስትር በስጡት የማጠቃለያ አስተያየት የዕለቱ መርሃ- ግብር የተጠናቀቀ ሲሆን በቀሪዎቹ ቀናትም በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የፓናል ውይይት ከኤግዚቪሽኑ ጎን ለጎን የሚካሄድ ይሆናል።

Posted in: ዜና