ህዳር 20, 2025
ሠመራ ሎጊያ ህዳር 10/2018
ከህዳር 6 ጀምሮ በሠመራ ሎጊያ ከተማ ሲከናወን የቆየው
10ኛው የኢትዬጵያ ከተሞች ፎረም በዛሬው እለት የኢፌድሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የአፋር ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት ክቡር ሀጂ አወል አርባ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዲሁም የተሳታፊ ከተሞች ተወካዬች በተገኙበት የመዝጊያ መርሀ ግብር ፍጻሜውን አግኝቷል።
ላለፉት አራት ተከታታይ ቀናት ከተሞች ራሳቸውን በማስተዋወቅ ረገድ በተለያዩ ምድቦች ባደረጉት ውድድር አሸናፊ የሆኑ ከተሞችን በመሸለም መርሀ ግብሩ ተጠናቋል። በተለያዩ ምድቦች በተደረጉ ውድድሮች አሸናፊ የሆኑ ከተሞች የሰርተፍኬት፣ የዋንጫ እና እንደየ ደረጃቸው የተለያየ መጠን ያላቸውን ቴሌቪዥኖችን ተሸልመዋል።
በዚሁ መሰረት:-
በምድብ 5 ከተሞች መካከል በተደረገ ውድድር
የወንዶ ገነት ከተማ 1ኛ፣
የመቂ ከተማ 2ኛ እና
ያዬ ከተማ 3ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነዋል ።
በምድብ 4 ከተሞች መካከል በተደረገ ውድድር
ኢንሴኖ ከተማ 1ኛ፣
አለም ገበያ 2ኛ እና
በደሌ ከተማ 3ኛ በመውጣት ሽልማት ተቀብለዋል።
በምድብ 3 ከተሞች መካከል በተደረገ ውድድር
ቡታጅራ ከተማ 1ኛ፣
ሆለታ ከተማ 2ኛ እና
ወልቂጤ ከተማ 3ኛ በመውጣት ተሸልመዋል።
በምድብ 2 ከተሞች መካከል በተደረገ ውድድር
ጅማ ከተማ 1ኛ፣
ሆሳዕና ከተማ 2ኛ እና
ዲላ ከተማ 3ኛ በመውጣት ሽልማት ተቀብለዋል።
በምድብ 1 ከተሞች መካከል በተደረገ ውድድር
አዳማ ከተማ 1ኛ፣
ቢሾፍቱ ከተማ 2ኛ እና
ሀዋሳ ከተማ 3ኛ በመውጣት አጠናቀዋል።
የኢትዬጵያ ከተሞች ፎረምን ለማዘጋጀት ፕሮፖዛል አቅርበው በዳኞች መስፈርት መሰረት አሸናፊ የሆነችው የቀጣዪ 11ኛው ፎረም አዘጋጅም የአሶሳ ከተሞ ሆና ተመርጣለች።
በመጨረሻም የሰመራ ሎጊያ ከተማ ለኢፌድሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ለከተማና መሰረተ ልማት ክቡራን ሚኒስትሮች ልዩ ሽልማት በማበርከት የእለቱ መረሃ ግብር በስኬት ተጠናቋል።