አርባምንጭ፣ የካቲት 13/2017 ዓ/ም
የኢፌዲሪ ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በአርባምንጭ ከተማ በተሰሩና በቀጣይ በሚሰሩ የልማት ሥራዎች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የመስክ ምልከታ እና ውይይት አካሂደዋል ።

ሚንስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በአርባ ምንጭ ከተማ የተሠሩና እየተሠሩ ያሉ የኮሪደር ልማት እና መሠረተ ልማት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቅሰው ሥራዎች በጊዜ እንዲጠናቀቁ የቅንጅት ሥራ ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል።

ለከተሞች ዕድገት ገቢ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው የገቢ መጠን ከፍ ለማድረግ የአሰባሰብ ዘዴን ማዘመን አስፈላጊ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

የአረንጓዴ ልማት ሥራ በተቀመጠው አሠራር መሠረት በትኩረት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋል ።

በከተማው የሚሠሩ ሥራዎች የመልካም አስተዳደር ችግር ጥያቄ ሊያስነሳ በማይችል መልክ መሆን እንዳለበትና በተለይ የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ከተማዋ ከፍተኛ የዕድገት ለውጥ እንድታሳይ የፌደራልና የክልል አካላት ድጋፍ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረው በዘርፉ በጥንካሬ የተመዘገቡትን አጠናክሮ በማስቀጠል ያጋጠሙ ችግሮችን እና ተግዳሮቶችን በመለየት ቀጣይ በትኩረት ሊሰራ እንደምገባ አጽንኦት ስጥተዋል ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ።አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን)

Posted in: ዜና