ህዳር 26, 2024

በመኖሪያ ቤት ግንባታ ዲዛይን ዝግጅትና በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ላይ ትኩረቱን አድርጎ በደቡብ ክላስተር ለሚገኙ 4 ክልሎች (ሲዳማ፤ ማእከላዊ ኢትዮጵያ፤ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ) በሐዋሳ ከተማ በተሰጠ የአቅም ግንባታ የስልጠና መድረክ ላይ ክልሎችም ተሞክሯቸውን አቅርበዋል፡፡

የሐዋሳ ከተማ ካቀረባቸው ተሞክሮዎች መካከልም በዋናነት በሐዋሳ ከተማ በማህበራት የተገነቡ ቤቶች ምርጥ ተሞክሮ ሆኖ ቀርቧል፡፡ የተገኙ ልምዶች ላይ በመመስረት በማህበራት ለተደራጁ አካላት በተሰጠ ቦታ ላይ የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ የመኖሪያ ቤቶች እና የመከላከያ ህንጻ ግንባታ በዛሬው ዕለት ህዳር 13/2017 ዓ.ም ከፌዴራል ከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር እና ከአራቱም ክልሎች በተውጣጡ ተሳታፊዎች ተጎብኝተዋል፡፡

Posted in: Uncategorized ዜና