የከተማ ልማት ሚኒስቴር አመሰራረትና የሥራ ኃላፊዎች በቅደም ተከተል

መግቢያ

በአመሰራረቱ የሥራ ሚኒስቴር ተብሎ የተሰየመው መስሪያ ቤት ከ 1889 ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ የመጀመሪያዎቹ
የካብኔ ሚኒስትሮች ሲቋቋም በመስራችነትም አንዱ ሆኖ በታሪክ ሰነዶች ተመዝግቦ ይገኛል። ይህ አንጋፋ
መንግስታዊ ተቋም 116 ዓመታትን ውጣ ውረድ ተጉዞ በማዘመን እዚህ ደርሷል። በዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ
ዘመን መንግስታዊ ሥራዎችን ለማዘመን እንዲረዳ ታስቦ የሚኒስትሮቹ ምክር ቤት ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር
ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርስ ዲነግዴ ሆነው ሹመት ተሰጣቸው።

የሥራ ሚኒስቴር (ከ1900 .ም – 1928 .) በተለያዩ ጊዜያት የስያሜ ለውጥ ሲያደረግ የቆየ ሲሆን
ድርሻው የከተማ ቦታን፣ መንገድና ውኃ ዝርጋታዎችን፣ ድልድይ ግንባታንና የማዘጋጃ ቤታዊ ኁነቶችን
የማስተዳደርና የመከታተል ኃላፊነት ነበር። በፋሽት ኢጣልያ ወረራ ዘመን (ከ 1928 .ም – 1933 .) ተጠሪነቱ
ሮም ከሚገኘው የሥራ ሚኒስቴር የአቢሲኒያ አዲስ አበባ ጎቨርነሬት (ቪስሮይ) ይወከል የነበረ ሲሆን ከተሾሙት
መካከል ኤንሪኮ ቸሩሊ እና ጁሊሞ ናዚ የተሰኙ ተሿሚዎች ይጠቀሳሉ። ከ1933 .ም እስከ 1935 .ም ባለው
ጊዜ ደግሞ ሀገራችን በእንግሊዝ ሞግዚትነት የቆየበት ወቅት ነበር።

ከ1935 .ም – 1950ዎቹ ባሉት ጊዜያት ደግሞ እንደ አዲስ የሥራና መገናኛ ሚኒስቴር በሚል ሲቋቋም
በዋናነት የከተማ ቦታ ልማት፣ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የመንገድ ትራንፖርትና ሲቪል አቬሽን ሥራዎችን የሚመሩ
ዲሬክተሮች አካቶ በመያዝ ነበር። አልፎ አልፎ በሀገር ግዛት ሚኒስቴር ሥር የማዘጋጃ ቤቶች ዋና ማደራጃ ሥር
የከተሞች ፕላን ሥራዎችን እንዲከናወን ይደረግ የነበረበት ሁኔታም ነበር። ቀጥሎም ከ 1966 .ም አብዮት
የሥርዓት ለውጥ ወዲህ ስያሜው የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር እንዲሁም የከተማና ቤት ሚኒስቴር እየተባለ
ሲጠራ ቆይቷል። ከ1994 ዓ.ም – 1998 ዓ.ም በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሥር በምክትል ሚኒስቴር ማእረግ ሹመት ይመራ ነበር። በኋላም ራሱን ችሎ የሥራ የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በሚል ተሰይሟል። ከ 1998 .ም – 2008 .ም ድረስ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር በሚል ተሰይሟል፡፡ ከ2008
.ም – 2010 .ም የከተማና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እንዲሁም ከ2010.ም – 2014 .ም ድረስ የከተማ
ልማት ሚኒስትር እንዲሁም ከ 2015 .ም ወዲህ ደግሞ በተሻሻለው የማቋቋሚያ ስያሜ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እየተባለ ይጠራል።

የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴርን በኃላፊነት እንዲመሩ የተሾሙት ባለሥልጣናትም በቅደም ተከተላቸው መሰረት እንደሚከተለው ስማቸው ይጠቀሳል።

Our History

  • 462775314_858550989791613_2659460802175017888_n
  • አመራሮች ከ (1900 - 1910 ዓ.ም)

    - ክቡር ቀኛዝማች መኮንን ተወንድበላይ (የሥራ ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር ደጃዝማች በየነ ይመር (የሥራ ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር ደጃዝማች መታፈሪያ መልከጻዲቅ (የሥራ ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር ፊታውራሪ ታፈሰ ሀብተሚካኤል (የሥራ ሚኒስቴር ሚኒስትር)

  • የፋሺስት ኢጣልያ ወረራ ዘመን (ከ 1928 ዓ.ም – 1933 ዓ.ም)

    በዚህ ወቅት ሮም በሚገኘው የሥራ ሚኒስቴር ሥር የአቢሲኒያ–አዲስ አበባ ጎቨርነሬት(ቪስሮይ) ማዘጋጃ ቤታዊ ተግባራትን ጨምሮ የከተማ ቦታና ቀረጥ፣ መንገድ፣ ድልድይ፣ ውኃ ዝርጋታ የመሳሰሉትን ተግባራት ይመራ ነበር።

  • 245540832_3927359837364615_6096727229179113508_n
  • transport service
  • የእግሊዝ ሞግዚትነት ዘመን (ከ 1933 ዓ.ም – 1933 ዓ.ም)

    በዚህ ወቅት በእንግሊዝ ሞግዚትነት መንግስታዊ ሥራዎች ከፊል ቁጥጥር ይደረግበት ነበር።

  • 1935 - 1938

    1934

    - ክቡር ብላታ ዘውዴ በላይነህ (የሥራና መገናኛ ሚኒስቴር ዋ/ሚኒስትር)
    - ክቡር ባላምባራስ ማኅተመሥላሴ ወልደመስቀል (የሥራና መገናኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴ (የሥራና መገናኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር ኮሎኔል አበበ ከበደ (የሥራነ መገናኛ ሚኒስቴር ዋና ዲሬክተር)
    - ክቡር ደጃዝማች መንገሻ ስዩም (የሥራና መገኛኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር አቶ ዮሐንስ ወልደገሪማ (የሥራ ሚኒስቴር ረ/ሚኒስትር)
    - ክቡር አቶ ንጉሴ ግዛው (በሥራና መገናኛ ሚኒስቴር ዋና ዲሬክተር)
    - ክቡር ዶክተር ኃይለጊዮርጊስ ወርቅነህ (የሥራና መገኛኛ ሚኒስቴር ሚኒስርት)
    - ክቡር ጓድ ዳንኤል ታደሠ (የሥራና መኖሪያ ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር)

  • 453874469_810930604553652_2263935625410281278_n
  • 453631677_810931321220247_363034545046499348_n
  • 2000 - Present

    - ክቡር ጓድ ዶክተር ካሳ ገብሬ (የከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር ጓድ ተስፋዬ ማሩ (የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር ጓድ ታደሠ ኪዳነማርያም (የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር ጓድ አራጋው ጥሩነህ (የቤቶች ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር አቶ ኃይሌ አሰግዴ (የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር አቶ አባይ ፀሐዬ (የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፤ ክቡር አቶ ብርሃኑ ታምራት የከተማ ልማት)
    - ክቡር ዶክርተር ካሱ ኢላላ (የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር አቶ መኩሪያ ኃይሌ (የከተማ፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር ዶክተር አምባቸው መኮንን (የከተማ ልማና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክቡር አቶ ጃንጥራር ዓባይ (የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    - ክብር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ (የከተማና ኮንስራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር)
    -ክብርት ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ (የከተማ መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር)

  • ማጠቃለያ

    ከአንድ ምዕተ ዓመት ባላይ እድሜ ያስቆጠረው የቀድሞው የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴርን የአሁኑ የከተማና መሠረተ ልማተ ሚኒስቴርን በተለያዩ ጊዜያት የመሩ ኃላፊዎችን ማስታወስ ተቋሙ ከየት ወዴት የታሪክ እድገት ጉዞ ለመገንዘብ ያስችላል። ይህ አንጋፋ ተቋም የሀገራችን ከተሞች በዘመናዊ ፕላን አሰራር ማሳደግና ልዩ ልዩ አገልግሎትን አሟልተው ከነዋሪው እድገትና ሁለገብ ፍላጎት አኳያ ምቹ እንዲሆኑ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል። በዚህም ዘመኑን የሚዋጁ ከተሞችን ማስፋፋትና የከተማና ቦታን መሠረተ ልማት ትስስር በአግቡቡ ጥቅም ላይ በመዋል የማዘመን ፈርን በማስቀጠል የበኩሉን ታሪካዊ ሚና ቀጥሏል።

  • 3