ተግባርና ኃላፊነት/ Duties & Responsibilities
የዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 133/2ዐዐ3 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስልጣንና ተግባራት አሉት ፡፡
- በክልሉ የሚካሄዱ ግንባታዎች ተገቢውን የዲዛይን መስፈርት ጠብቀው መዘጋጀታቸውን አጠቃላይ ቁጥጥር ያደርጋል፤
- የፌደራልና የክልሉ ኮንስትራክሽን ፖሊሲዎችና የግንባታ ኮዶች መከበራቸውን ያረጋግጣል፤
- በክልሉ ለሚካሄዱ ግንባታዎች መመሪያች ማኑዋሎችን የአሰራር ሥርዓቶችን ያዘጋጃል ይተገብራል፤
- በግንባታ ለሚሰማሩ ባለሙያዎችና ሥራ ተቋራጮች አማካራዎች፤ የሙያ የሥራና የአማካሪነት ፍቃድ ይሰጣል፤ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ይሰርዛል፤
- በክልሉ መንግስት በጀት ለሚገነቡና በአማካሪዎች ቁጥጥር ለሚደረግባቸው ግንባታዎች የሚቀርቡ ክፍያዎች አሰሪ መ/ቤቶች በመወከል ክፍያ ያፀድቃል፤
- ከክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤትና ከሌሎች መ/ቤቶች ለሚቀርቡ አነስተኛ ግንባታዎች የምህንድስና ግምት ያዘጋጃል፤
- የአነስተኛ ግንባታዎች ውለታ ማስተዳደር ሥራ ያካሂዳል፤
- በግንባታ ሂደት በአሰሪ መ/ቤቶች፤ በአማካሪና በሥራ ተቋራጭ መካከል ለሚነሱ አለመጋባባቶች መፍትሄ ይሰጣለ፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- በአማካሪዎች ወይም በሌላ አካል ለሚሰሩ ዲዛይኖች የመወዳደሪያ ዝክር ተግባር ያዘጋጃል፤ የአማካሪ ደረጃ ይወስናል፤
- በክልሉ የሚካሄዱ ማናቸውም ግንባታዎች ጥራት ቁጥጥር ያካሂዳል፤
- ለተቋራጭ በተጨማሪ ለሚሰጡ ሥራዎች የሚቀርቡ ዋጋ ይመረምራል፤ ተገቢነታቸውን ያረጋግጣል፤