Web Content Display Web Content Display
Minimize Maximize

መሬት በኢኮኖሚ ውስጥ ገብቶ የበኩሉን ሚና እንዲጫወትና ከመሬት ጋር ተያይዞ  የሚፈጠረውን የኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ የመሬት መረጃ የአሠራር ስርዓት በዘመናዊ ቴኖሎጂ ሊታገዝ ይገባል፡፡ ሲሉ የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር አቶ መለሠ ዓለሙ አሣሠቡ፡፡

የመሬት መረጃ የአሠራር ስርዓት በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ  በአምስት ትልልቅ ከተሞች  ትኩረት ተሠጥቶት እየተሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ዝርዝሩ እንደሚከተለው

የከተማ መሬት መረጃ በአግባቡ ባለመመዝገቡና ባለመደራጀቱ የአገልግሎት አሠጣጡ እንዳይሣለጥ፣ የባለይዞታዎች ቦታና ንብረት ዋስትና እንዳይረጋገጥ፣ ለሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ መበራከትና ከመሬት ጋር ተያይዞ ለሚሰጡ አስተዳደራዊና ሕጋዊ ውሣኔዎች ጥራት መጓደል ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መምጣቱ ተገለጸ፡፡

የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደርና የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሠ ዓለሙ እንደተናገሩት፣ መሬት በከተሞች የሚጠበቅበት፣ የሚለማበትና የሚተዳደርበት ፖሊሲ፣ የሕግ ማዕቀፎችና የአሠራር ሥርዓቶች ለኪራይ ሠብሣቢነት በር በማይከፍትና ለልማት በሚውል ደረጃ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ባለመደገፉ ያለበት ደረጃ አሣሣቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም መሬት በኢኮኖሚ ውስጥ ገብቶ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለማድረግና ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚከሠቱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የአመለካከት ግንባታ ሥራው በአሠራር ሥርዓት እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሊታገዝ ይገባል ሲሉ ም/ርዕሰ መስተዳድሩ አሣስበዋል፡፡

በከተሞች ውስጥ ከሚንቀሣቀሠው ካፒታል ትልቁን ድርሻ የሚይዘው መሬት አንደሆነ የተናገሩት አቶ መለሠ፣ ለምርታማነትና ለአገልግሎት በማዋል የማምረቻ ኢንዱስትሪ ስራዎችን በከተሞች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡

በዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን ለማሣካትና የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ አመራሩ፣ ባለሙያውና ሕዝቡ ንቁ ተሣትፎ በማድረግ የሥራው ባለቤት ሊሆን ይገባል ሲሉም ም/ርዕሰ መስተዳድሩ መልክት አስተላልፈዋል፡፡

በከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ አያኖ ሱመኖ በበኩላቸው፣ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ስርዓት ጊዜ የማይሠጠው ጉዳይ እንደሆነ አመላክተው፣ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓቱን በማዘመን ከተሞች ያላቸውን የመሬት መጠን ለይተው እንዲያውቁና ለሌሎች የልማት ሥራዎች ምቹ ሁኔታን እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

አቶ አያናው በመቀጠልም በክልሉ ለመጀመሪያ  ጊዜ በአምስት ትልልቅ ከተሞች የመሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ የቅድመ ዝግጅት ሥራው እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በከተሞች የመሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ለመጀመር በሚደረገው ጥረት የቅድመ ዝግጅት ሥራው ያለበት ደረጃም ተገምግሟል፡፡

ህገ ወጥ ግንባታን ስርዓት ከማስያዝ፣ድንበር ከማካለል፣ነባር የይዞታ መረጃዎችን ከማደራጀት፣ የሰው ሃይል ልማቱንና ቁሳቁሱን ከማሟላት አንጻር አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውንና በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ እንደሚገኙ የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

Web Content Display Web Content Display
Minimize Maximize

በከተሞች የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች በአግባቡ አለመያዝና አለመወገድ የአየር ንብረት ለውጡን ከማዛባቱ በላይ በማህበራዊና ኢኮኖሚየዊ ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ የከፋ መሆኑን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ 

የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሥርዓቱ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ አለመሆን የአለምን የሙቀት መጠን 5 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጎታል፡፡ 

በጉዳዩ ዙሪያም ለባለድርሻ አካላቱ ስልጠና ተሠጥቷል፡፡

ዝርዝሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በከተሞች በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ችግር የሚፈጠሩ የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች ለሙቀት መጠን መጨመር ከፍተኛ መንስኤ መሆናቸው ተገለፀ ፡፡

በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር፣ በከተሞች ኘላን ፣ጽዳትና ውበት  ቢሮ፣ የከተሞች ጽዳት አገልግሎትና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የፊዚካልና ኢንቫይሮመንታል ኤክስፐርት አቶ ሰመረ ገ/ፃዲቅ እንደተናገሩት ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ለመገንባት ከከተሞች በሚመነጩ የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች አያያዝና አወጋገድ ተግባራት ላይ ከተሞች በስታንዳርዱ መሠረት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

አሣሣቢነቱ እየከፋ የመጣውንም ችግር ከወዲሁ ለማስወገድ በከተሞች አካባቢያዊ ጉዳዩች ላይ በወጡ ስትራቴጂዎች ፣ ፖሊሲዎች፣ የሕግ ማዕቀፎችና ስታንዳርዶች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ መሆን እንዳለባቸው አቶ ሠመረ አሳስበዋል፡፡

በዚህም ልክ ከተሞችን ማስተዳደር ከተቻለ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን በማፋጠንና የሕዝቡን ደህነት በማረጋገጥ ወደ ብልጽግና ማምራት እንደሚቻልና ቆሻሻን በአግባቡ በመያዝና ወደ ሃብት በመቀየር ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠርም ባሻገር በግብርናው ዘርፍ ለምንፈጥረው ትራንስፎርሜሽን አጋዥ እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡ 

 አቶ ሰመረ ገ/ፃዲቅ   

በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር፣ በከተሞች ኘላን ፣ጽዳትና ውበት ቢሮ፣ የከተሞች ጽዳት አገልግሎትና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የፊዚካልና ኢንቫይሮመንታል ኤክስፐርት

 አሣሣቢነቱ እየከፋ የመጣውንም ችግር ከወዲሁ ለማስወገድ በከተሞች አካባቢያዊ ጉዳዩች ላይ በወጡ ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎች፣ የሕግ ማዕቀፎችና ስታንዳርዶች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ መሆን እንዳለባቸው አቶ ሠመረ አሳስበዋል፡፡

በዚህም ልክ ከተሞችን ማስተዳደር ከተቻለ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን በማፋጠንና የሕዝቡን ደህነት በማረጋገጥ ወደ ብልጽግና ማምራት እንደሚቻልና ቆሻሻን በአግባቡ በመያዝና ወደ ሃብት በመቀየር ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠርም ባሻገር በግብርናው ዘርፍ ለምንፈጥረው ትራንስፎርሜሽን አጋዥ እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡

በክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ፣ የከተሞች ጽዳት አስተዳደርና አረንጓዴ ልማት ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ በጎነት ዳሌ በበኩላቸው ፣ ከተሞች ከነበሩበት ኋላ ቀር የዕድገት ደረጃ ለመላቀቅና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለአየር ንብረት ለውጥ መንስኤ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሠፊ ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

አቶ በጎነት ዳሌ

በክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ፣ የከተሞች ጽዳት አስተዳደርና አረንጓዴ ልማት ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት  

በየቦታው የሚጣሉ ቆሻሻዎች ለላይኛውና ለከርሰ ምድር ውሃ ብክለት የሚያጋልጡ ሲሆን በተለይም ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ሞት መንስኤነት በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው ከሐይጅንና ከሳኒቴሽን ጉድለት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የጤና ችግር መሆኑን ለመድረኩ ተሣታፊዎች ተናግረዋል፡፡

ከማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ መስፋፋትና ከሕዝብ ቁጥር አድገት ጋር ተያይዞ እየተፈጠረ ያለውን የደረቅ ቆሻሻ ዓይነትና መጠን በሚገባ በመያዝና በማስወገድ የአየር ንብረት ለውጡን መቋቋምና ከተሞችን የደን ውስጥ ከተማ ማድረግ ይኖርብናል ነው ያሉት፡፡

 በስልጠናው የተገኙ ተሣታፊዎች

 ለዚህም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ ወሣኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በስልጠናው የተገኙት ተሣታፊዎች እንደተናገሩት ፣ የችግሩ አሣሣቢነት ጊዜ የማይሰጠው በመሆኑ ሕብረተሰቡና ባለድርሻ አካላቱ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸውና በመዋቅር ደረጃም የሠው ኃይል ልማቱና የቴክኖሎጂ ግብዓቱ ሊሟላ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡በተጨማሪ የከተማ ኘላን ሲዘጋጅ ለደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ መሠረተ ልማቶች ሊካተቱ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ 

የሀገሪቱን  የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ከግብ ለማድረስ የከተማ ኘላን ዝግጅትና ትግበራን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

 ይህ የተገለፀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ጋር በይርጋለም ከተማ በጋራ ባዘጋጁት የምክክር መድረክ ነው፡፡ 

የኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚው በከተሞች በሚስፋፋበት ወቅት የሚከሠተውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከተሞችን በኘላን በመምራትና በዕውቀት በመታገዝ ሊፈቱ ይገባል ተብሏል፡፡

በቅድመ ዝግጅት መድረኩ የሚኒስቴር መ/ቤቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ታረቀኝ ገብረክርስቶስ እንዳተናገሩት፣ የሃገራችን የከተሞች እድገት ፈጣን እንደመሆኑ መጠን በከተማ ኘላን ዝግጅትና ትግበራ ስትራቴጂ፣ በአረንጓዴ ልማት ፣ በዘርፋ በወጡ የሕግ መዕቀፎችና የአሠራር ስርዓቶች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ኢንዱስትሪውን ማስፋፋትና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጡን ማምጣት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
 
 አቶ ታረቀኝ ገብረክርስቶስ  የሚኒስቴር መ/ቤቱ አስተባባሪ   

ዘርፋን ውጤታ ለማድረግ የከተማ ኘላን ዝግጅትና ትግበራ የሚደግፍና የሚያስፈፅም ተቋም በየደረጃው መፈጠር እንዳለበት አመላክተው፣ ሙያዊ ሥነ ምግባር የተላበሠ አመራርና ባለሙያ በማፍራት፣ የግሉን ዘርፍና የህዝቡን ተሣትፎ በማጠናከር የተፈለገውን ግብ ማሣካት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የከተሞች ፕላን አደረጃጀት ዝግጅትና ክትትል  ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሐሣሞ ሐሪሶ በበኩላቸው ፣ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት ስኬታማ ለማድረግ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ተቀናጅቶ መስራቱ የጎላ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፣የክልላችን ከተሞች ያላቸውን የእድገት ደረጃ በጥራት ለማሳደግና ለኢንቨስትመንት ዘርፉ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የከተማ ፕላናቸውን በሚገባ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

አቶ ሐሣሞ ሐሪሶ 

የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የከተሞች ፕላን አደረጃጀት ዝግጅትና ክትትል  ዋና የስራ ሂደት ባለቤት 

አቶ ሀሳሞ አክለውም የከተሞች በፕላን አለመመራት ለተለያዩ መሰረተ ልማት ተግዳሮት ከመሆኑም በላይ ለህገ ወጥ የመሬት ወረራና ኪራይ ሰብሳቢነት ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸው አብራርተው፣ በዘርፉ የሚታየውን የኘላን ጥሰት ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከመቼው ጊዜ በላይ ቁርጠኛ አቋም ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በቅድመ ዝግጅት መድረኩ የክልል ፣የዞን፣ የከተማና የወረዳ ከተማ ልማትና ቤቶች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆች የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ አስተያየቶችም ተነስተዋል፡፡ በዋናነት ህዝቡን ያሳተፈ የኘላን ዝግጅት ያለመኖር ፣ የፈፃሚው ብቃት ያለመጎልበት ፣የአመራሩ

ግንዛቤና ቁርጠኝነት ማነስ መኖሩን በምክንያትነት ጠቅሰው፣ ለአመራሩና ለባለሙያው የጋራ መድረክ መዘጋጀቱ ለዕቅዱ ስኬት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል፡፡

ተሳታፊዎች እንደተናገሩት፣መድረኩ ቀደም ሲል በኘላን ዝግጅትና ትግበራ ወቅት የሚታየውን ውስንነትና ጥንካሬ እንድንገነዘብ ከማስቻሉም በላይ ከከተማ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ አንፃር የክልላችን ከተሞች ያሉበትን ደረጃና እድገት ለማየትና ከተሜነት በማስፋፋት የመንግስት ፣የህዝቡንና የግሉን ዘርፍ በማጠናከር ልማቱ የሚፋጠንበትን ሁኔታ እንድናመቻች ያግዘናል ብለዋል፡፡

የከተሞችን መስፋፋትና ማደግ ተከትሎ ከተሞችን በኘላን መምራት የበለጠ አስፈላጊና ወቅታዊ የልማት አጀንዳ በመሆኑ በሰፋፊ ከተሞች ዙሪያ ያሉትን አነስተኛ ከተሞችና ከተማ ቀመስ የገጠር አከባቢዎች በማካተት የቀጣይ አመታት የልማት ራዕይ ባገናዘበ መልኩ እንድናዘጋጅ ያስችለናል ነው ያሉት፡፡በመጨረሻም በከተማ ኘላን ዝግጅት ፣ በከተማ እውቅና ጥናት ፣ በቦታ ደረጃና በመሰረታዊ ኘላን ዝግጅት ላቅ ያለ ውጤት ላስመዘገቡ የጉራጌ ፣ የወላይታና የሀዲያ ዞኖች በቅደም ተከተላቸዉ ደረጃ የእውቅና ሽልማት የተሰጣቸው ሲሆን የስኬች ኘላንን በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ የሆሳዕና ከተማ ተሸላሚ ሆኗል ሲል ፡፡  በከተሞች የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች በአግባቡ አለመያዝና አለመወገድ የአየር ንብረት ለውጡን ከማዛባቱ በላይ በማህበራዊና ኢኮኖሚየዊ ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ የከፋ መሆኑን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ 

የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሥርዓቱ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ አለመሆን የአለምን የሙቀት መጠን 5 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጎታል፡፡  

በጉዳዩ ዙሪያም ለባለድርሻ አካላቱ ስልጠና ተሠጥቷል፡፡

ዝርዝሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ 

በከተሞች በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ችግር የሚፈጠሩ የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች ለሙቀት መጠን መጨመር ከፍተኛ መንስኤ መሆናቸው ተገለፀ ፡፡

በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር፣ በከተሞች ኘላን ፣ጽዳትና ውበት  ቢሮ፣ የከተሞች ጽዳት አገልግሎትና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የፊዚካልና ኢንቫይሮመንታል ኤክስፐርት አቶ ሰመረ ገ/ፃዲቅ እንደተናገሩት ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ለመገንባት ከከተሞች በሚመነጩ የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች አያያዝና አወጋገድ ተግባራት ላይ ከተሞች በስታንዳርዱ መሠረት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

አሣሣቢነቱ እየከፋ የመጣውንም ችግር ከወዲሁ ለማስወገድ በከተሞች አካባቢያዊ ጉዳዩች ላይ በወጡ ስትራቴጂዎች ፣ ፖሊሲዎች፣ የሕግ ማዕቀፎችና ስታንዳርዶች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ መሆን እንዳለባቸው አቶ ሠመረ አሳስበዋል፡፡

በዚህም ልክ ከተሞችን ማስተዳደር ከተቻለ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን በማፋጠንና የሕዝቡን ደህነት በማረጋገጥ ወደ ብልጽግና ማምራት እንደሚቻልና ቆሻሻን በአግባቡ በመያዝና ወደ ሃብት በመቀየር ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠርም ባሻገር በግብርናው ዘርፍ ለምንፈጥረው ትራንስፎርሜሽን አጋዥ እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡

በክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ፣ የከተሞች ጽዳት አስተዳደርና አረንጓዴ ልማት ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ በጎነት ዳሌ በበኩላቸው ፣ ከተሞች ከነበሩበት ኋላ ቀር የዕድገት ደረጃ ለመላቀቅና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለአየር ንብረት ለውጥ መንስኤ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሠፊ ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በየቦታው የሚጣሉ ቆሻሻዎች ለላይኛውና ለከርሰ ምድር ውሃ ብክለት የሚያጋልጡ ሲሆን በተለይም ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ሞት መንስኤነት በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው ከሐይጅንና ከሳኒቴሽን ጉድለት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የጤና ችግር መሆኑን ለመድረኩ ተሣታፊዎች ተናግረዋል፡፡

ከማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ መስፋፋትና ከሕዝብ ቁጥር አድገት ጋር ተያይዞ እየተፈጠረ ያለውን የደረቅ ቆሻሻ ዓይነትና መጠን በሚገባ በመያዝና በማስወገድ የአየር ንብረት ለውጡን መቋቋምና ከተሞችን የደን ውስጥ ከተማ ማድረግ ይኖርብናል ነው ያሉት፡፡

ለዚህም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ ወሣኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው የተገኙት ተሣታፊዎች እንደተናገሩት ፣ የችግሩ አሣሣቢነት ጊዜ የማይሰጠው በመሆኑ ሕብረተሰቡና ባለድርሻ አካላቱ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸውና በመዋቅር ደረጃም የሠው ኃይል ልማቱና የቴክኖሎጂ ግብዓቱ ሊሟላ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪ የከተማ ኘላን ሲዘጋጅ ለደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ መሠረተ ልማቶች ሊካተቱ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡