የመሬት ልማት እና ሜኔጅመንት ጽ/ቤት

 

   መግቢያ

መሬት ዉስን ሀብት በመሆኑ መሬትን በአግባቡ ከኪራይ ሰብሳቢነት በማጽዳት ለአገሪቱ ልማት ወሳኝ ሚና መጫወት እንድቻል የማድረግን አሰፈላጊነት መንግስት በመገንዘብ ከ2000ዓመት ምህረት ጀምሮ መሬት ልማትና አሰተዳደር ስራ ሂደት ተዋቅሮ ሥራዎች ተገልጋይ ተኮር በሆነ መልኩ ስተገበር ቆይቷል፡፡

 

ይሁን እንጂ በመሬት ልማትና አሰተዳደር ዘርፍ ቀደምት ከነበሩ መንግስታት ወቅት ጀምሮ  ዉዝፍ ስራዎች በሰነደ አልባ ይዞታዎቸ፣ በህገወጥ ይዞታዎቸ ፣ የመረጃ አደረጃጀት ችግሮችና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች መኖራቸዉና የመሬት ፍላጎት በየወቅቱ እየጨመረ  ከመሄዱ ጋር ተያይዞ የመሬት አሰተዳደሩ ስራዎች እየተሰተካከለ ከመሄድ ይልቅ የበለጠ በመወሳስብ የክራይ መሰብሰቢያ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን መገንዘብ ተችሏል፡፡ ስለዚህ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመሰጠት የመሬት ዘርፍ ፖሊሲ ጭምር እንድፈተሸ በማድረግ ከፖሊሲዉ ጀምሮ መሉ መዋቅራዊ ለዉጥ እንዲደረግ በመወሰኑ አጠቀላይ አደረጃጀቱን የመፈተሸ ተግባር ተከነዉኗል፡፡

 

በተጨማርም መንግስት በዘርፉ የሚታየውን ኪራይ ሰብሳቢነት በመድፈቅ ለልማትና ልማታዊነት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ግልፅ ፖሊሲ፣ስትራቴጅናና የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን በማውጣት ተጨባጭ እንቅስቃሴ እያደረገ በመሆኑ፣እንዲሁም ክፍለ ኢኮኖሚያዊ የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከማሳካት አንፃር ከፌደራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር ጋር የተናበበ አደረጃጀት በመፍጠር ዘርፉን በሰው ኃይል ማጠናከር በማስፈለጉ ፖሊሲዉን ተከትሎ ክልላችን የመሬት ዘርፉን አደረጃጀት በመሬትና መሬት ነክ መረጃ ምዝገባ  አጀንሲ፣መሬት ልማትና ማነጅመንት ፅ/ቤት እንዲሁም የተቀናጀ የመሬት መረጃ ስርዓት ዝርጋታ ፕሮጀክት ፅ/ቤት በሚል አዋቅሯል፡፡ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም የካዳስተር የሥራ ሂደት የሚባለዉ በሁለት ተከፍሎ የመሬት መረጃ ወደ መሬት ልማትና ማኔጅመንት፣የቋሚ ንብረት ምዝገባዉ በመሬትና መሬት ነክ መረጃ ምዝገባ ኤጀንሲ የሚተገበር በመሆኑ አደረጃጀቱንና የሰዉ ኃይሉን በዚህ አግባብ ፈጥኖ በማስተካከል የሰዉ ኃይል በሟሟላት ወደ ተግባር እየተገባ ይገኛል፡፡