የኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ

 

የኤጀንሲው ተልዕኮ፡

በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለተሰማሩና ለሚሰማሩ ተገልጋዮች የአደረጃጀት፣ የሥልጠናና የምክር አገልግሎት ማመቻቸት፣ የመሥሪያ የመሸጫ ቦታና ቤት አቅርቦት ማመቻቸት፣ የብድር አቅርቦት ማመቻቸት፣ የማምረቻና ተስማሚ ቴክኖሎጂ አቅርቦት ማመቻቸትና የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመስጠት፣ ቁጠባን ሞቢላይዝ በማድረግ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ኢንተርፕራይዞችን ማብቃት ነው፡፡

የኤጀንሲው ራዕይ፡

በ2012 ዓ.ም በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓት ያላቸው፣ በገበያ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ፣ ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት የላቀ ሚና የሚጫወቱ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተፈጥረውና የከተማው ሕዝብ የኑሮ ደረጃ ተሻሽሎ ማየት፡፡

  

የኢንተርኘራይዞች ልማት ኤጄንሲ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡

1.   በክልሉ በተለይም በከተሞች ድህነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ  የጥቃቅንና አነስተኛ ሥራዎች የሚስፋፉበትን ስልት ይነድፋል፣ ይፈጽማል፣

2.   በክልሉ ሥራ አጥ ወገኖች በማኀበር እየተደራጁ በየሙያቸው የጥቃቅንና  አነስተኛ ኢንተርኘራይዞችን እንዲያቋቁሙ ያነሳሳል፣ ማኀበራትን ያደራጃል፣ ይደግፋል፣

3.   በክልሉና በየከተማው ካለው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት የተለየ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ዘርፎችን ያጠናል፣ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ በፖኬጅ የሚያገኙበትን ኘሮግራምና ኘሮጀክቶች ይቀርፃል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ  ያደርጋል፣

4.   የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዞች ተጨባጭ ችግሮች በጥናት ይለያል፣ የሚፈቱበትን አቅጣጫ ይቀይሳል፣ ይተገብራል፣

5.   የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዞች ሁሉ አቀፍ ድጋፍ እንዲያገኙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጥበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ ያስተባብራል፣

 

Pages: 1  2  3  4  5  6  7  8  9  10  11  12