
June 24, 2025
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ሚኒስትር በክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ የልዑክ ቡድን በቢሾፍቱ ከተማ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መልሶ ማስፈር እና ማቋቋም የባለ 7 ወለል ቅይጥ ህንጻ ግንባታን አፈፃፀምን፣ የካም ሴራሚክ ፋብሪካን ግንባታ እና ቃሊቲ የሚገኘውን የኮርፖሬሽኑን የኢንዱስትሪ ዞን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኘ፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ኮርፖሬሽኑን ለስኬት ያበቁት ጉዳዮች፣ የነበሩ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ኮርፖሬሽኑ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ የኮርፖርሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ገለፃ አድርገዋል፡፡