
June 16, 2025
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ/ም (ከመልሚ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከአለም ባንክ በተደረገለት 7.2 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ የክልሎችን ክልላዊ ልማት ስፓሻል ፕላን ለUN-HABITAT በውል ስምምነት ሰጥቶ ባለፉት ሶስት አመታት እንዲያዘጋጅ ክትትል እና ድጋፍ ሲያደረግ የቆየ ሲሆን የዘጠኝ ክልሎች ጥናት በማጠናቀቅ ጥናቱን እና ለሥራው የተገዙ ላፕቶፖችን ርክክብ አደረገ፡፡
በርክክቡ ወቅት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን እንዳሉት ክልሎች የስፓሻል ፕላን ጥናት ለማካሄድ አቅምና ፋይናንስ ስላልነበራቸው ከአለም ባንክ በተደረገልን 7.2 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ዩኤን ሀቢታት ጥናቱ እንዲያጠና በማድረግ የዘጠኝ ክልሎች ጥናት አጠናቋል።
ጥናቱ በክልሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘው ተናግረዋል፡፡
ሪፖርተር:- ኮከቤ ቢፍቱ
ፎቶግራፍ :-አስመላሽ ተፈራ