April 10, 2025

አዳማ፣ መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም (ከመልሚ) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ከኦሮሚያ ክልል ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ለተውጣጡ አስመራና ባለሙያዎች በመኖሪያ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ዙርያ በወጡ የህግ ማዕቀፎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅ  ቁጥር 1357/2017 እና የአዋጁ ደንብ ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ፣ እንዲሁም የቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 አስመልክቶ በአተገባበር ሂደት የነበሩ አሰራሮችን የሚያሳዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ በከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ትዕግስት ዓለሙ እንደተናገሩት በከተሞች ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የመኖሪያ ቤት እጥረት እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ ዜጎች ችግሩን ለመፍታት ሚኒሰቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ከመኖሪያ ቤቶች ጋር ተያይዞ ዘርፉን በከፍተኛ ደረጃ እየፈተኑት የሚገኙት የፋይናንስ እጥርት፣ አቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም፣ ዝቅተኛ የመሬት አቅርቦት፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አለመዘመን፣ የአመራርና የአደረጃጀት ችግር ዘርፉን እየፈተነው መሆኑን በቀረበው ሰነድ ላይ በዝርዝር ተመላክቷል።

በመጨረሻም ከቤቱ ለተነሱት ሀሳቦች ማብራሪያና በቀጣይ በሂደት የሚተገበሩ ዝርዝር የአሠራር ሥርዓቶች ቀርበዋል።

ዘጋቢ፡-ሞገስ ዓሊ
ፎቶ ባለሙያ፡-ፈየ ደሜ

Posted in: News