
October 21, 2025
አድስ አበባ ጥቅምት 07፣ 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የከተመና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች የብሔራዊ ጥቅም እና ጂኦስትራቴጂካል ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ።
ለውይይት በቀረበው ሰነድ የብሔራዊ ጥቅም ምንነት፣ የኢኮኖሚ ብልፅግና፣ ፖለቲካዊ አቅምና ተፅዕኖ ፈጣሪነት፣ የህዝቦች ማህበራዊ ልማት ማህበራዊ ዋስትና፣ ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትን፣ የባህር በር ጉዳይ፣ ሰላምና ጸጥታን ማረጋገጥ፣ ከፖለቲካ ሀይሎች ጋር ሰላማዊ አማራጭ መከተል የሚሉ ሀሳቦች ተዳሰዋል።
በአርበኝነት ስሜት የኢትዮጵያን አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር የሀገራችንን ህልውና ደኅንነት እና እድገት መወሰን እንደምገባን የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የከተሞች የምግብ ዋስትናና ሴፊቲኔት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ብርሀኑ ተሾመ ተናግረዋል ።
የእኛ የኢትዮጵያዊያን ዓለማ ብሔራዊ ፍላጎቶቻችንን ማወቅ፣ ሰላማችንን መጠበቅ፣ ተባብረን ከወንድም ጎረቤት ህዝቦች ጋር በጋራ መስራት አለብን ብለዋል አቶ ብርሀኑ።
በውይይት መድረኩ በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ክብርት ሚ/ዴኤታ ወ/ሮ ሄለን ደበበ በማጠቃለያቸው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሰላም እና አንድነት ለማረጋገጥ ሁላችንም በተሰማራንበት መስክ ውጤት ማስመዝገብ እና አንድ መሆን ከቻልን እንዲሁም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና የውስጥ ችግሮቻችንን በመፍታት ብልፅግናን ማረጋገጥ እንዳለብን ገልጸዋል።