
July 23, 2025
ቱሉ አራራ ፣ ሐምሌ 15፣2017 ዓ.ም (ከመልሚ) የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማት መላው አመራሮች የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎትና የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ‹‹በቱሉ አራራ ከተማ ›› ከኦሮሚያ ክልል በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር በጋራ አካሂደዋል፡፡
ይህ መርሃ-ግብር የተከናወነው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ሰበታ ሀዋሳ ወረዳ ሲሆን፣ 35 አባውራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሞዴል የገጠር ከተሞችን ታሳቢ ያደረገና አስፈላጊው ሁሉ መሠረተ-ልማት የተሟላላቸው መኖሪያ ቤቶችን በሦስት ወራት አጠናቆ ለተጠቃሚዎች ለማስረክብ በክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና ሁሉም አመራር በጋራ የመሠረተ ድንጋይ የማኖር እና ፕሮጀክቱን ማስጀመርያ መረሃ ግብር አከናውነዋል።
በተመሳሳይ የቱሉ አራራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን አራት የመማሪያ ክፍል ያላቸው ሁለት ብሎክ የመመሪያ ክፍሎችንና አንድ ቤተ-መጽሐፍን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ ገንብቶ ለተማሪዎች ለመጩ ዓመት የትምህርት ዘመን ለማድረስ እና የመማሪያ ቁሳቁሶች አሟልቶ ለማስረከብ እየተሠራ እንደሆነ ክብርት ሚኒስትር የትምህርት ቤቱን ግንባታ ባስጀመሩበት ጊዜ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የሚኒስቴር መስሪ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማት ሁሉም አመራሮች በተገኙበት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር 7ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ‹‹በመትከል ማንሰራራት›› በሚል መሪ ቃል ችግኞችን ተክለዋል፡፡
ሪፖርተር፡-ሞገስ ዓሊ
ፎቶግራፍ ፡- አስመላሽ ተፈራ