July 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ከ.መ.ልሚ.) የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን የከተማና መሠረተ-ልማት ሚ/ዴኤታ ክቡር አቶ የትምጌታ አስራት ከኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት በክር ሻሌ(ዶ/ር) እንዲሁም ከሔልቬትአስ የኢትዮጵያ ተወካይ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ብጽአት ሲሳይ ጋር የገጠር ትስስር እና ተደራሽነት ፕሮግራምን በቅንጅት መሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የፊርማ ስነ-ስርዓቱን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንደተናገሩት የመንግስት የማስፈጸም አቅም እያደገ በመምጣቱ የገጠር መንገዶችን ከቀበሌ እስከ ዋና መንገዶች ጋር በማስተሳሰር በገጠር የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ደረጃቸውን ከማሻሻልና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚዘረጉ የፕሮጀክት አፈጻጸሞችን በታማኝነትና በቅንነት ሪፖርቶችን በማረጋገጥ የሕብረተሰቡን የዘመናት ጥያቄዎች እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ(ዶ/ር) በበኩላቸው በተስማማንበት የመግባቢያ ሰነድ ቃላችንን አክብረን በየደረጃው የሚቀርቡ ሪፖርቶችንን ታዓማንነታቸውን በማረጋገጥ መንግሰትና ህዝብ የጣለብንን ሚናችንን በአግባቡ እንወጣለን ብለዋል፡፡

የሔልቬትአስ የኢትዮጵ ተወካይ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ብጻዓት ሲሳይ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ እንደተናገሩት በገጠሪቱ የሀገራችን ክፍሎች ተንጠልጣይ ድልድዮችን በመስራት በርካታ ዓመታት ልምዶቻችንን ተጠቅመን በምንገባው ውል መሠረት ቃላችንን አክብረን ፕሮጀክቱ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ ድርጅታቸው ከመንግስት ና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሠራ ቃል ገብተዋል፡፡

በሌላ በኩል የሚኒስቴር መ/ቤቱን ህንጻ በአዲስ መልክ ለስራ ምቹ፣ ውብና ማራኪ ለማድረግ ሲታደሱ የቆዩትን ቢሮዎች መጠናቀቃቸውን ተከትሎ አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ ባላደርሻ አካላት በተገኙበት ጉብኝ ተካሂዷል፡፡

በመጨረሻም በእድሳት ስራው ላይ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ድርጅቶችና ባለሙያዎች የዕውቅናና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ሪፖረተር፡-ሞገስ ዓሊ
ፎቶግራፍ ፡- አስመላሽ ተፈራ

Posted in: News