October 15, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከርም 28 ፣ 2018 ዓ.ም  (ከመልሚ) እ.ኤ.አ ከ2025-2050 ለሚቀጥሉት 25 ዓመታት  የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተግዳሮት እንደምፈታ የታመነበት የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭ ይፋ መደረጉ ይታወቃል፡፡

የኢኒሸቲቩ ዋና ማጠንጠኛ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ   እና የፋይናንስ ዕቅድ  ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቅ ማስቻል ነው፡፡

ይሄንኑ ታሳቢ ያደረገና ለኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭ  መሳካት የኢንዱስትሪው ተዋናዮች ከብልሹ አሰራር በመራቅ የጋራ እና የተናጥል ኃላፊነት በመውሰድ ፣ ለሚፀድቁ መመሪያዎች ተገዥ በመሆን መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ነው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚ/ድኤታ አቶ የትምጌታ አስራት እና የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዚዳንት እንጂ.የሱፍ መሀመድ የተፈራረሙት።

የስምምነት ሰነዱ  ለኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው እድገት የሚበጁ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ፣ የአሰራር ስርአቶችን ፣ እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ታሳብ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

Posted in: News