
October 15, 2025
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27/2018 ዓ.ም(ከመልሚ) የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሚሽን ኢንሼትቭ በቅርቡ ይፋ አድርጎ ወደ ተግባር የገባ መሆኑ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የዚሁ ኢንሼትቭ አካል የሆነውን የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ስራን በማዘመንና የዘርፉን የአሰራር ስርዓት በማሳለጥ የ2030 ዲጂታል ኢኮኖሚ ግብ ለማሳካት እንዲቻል የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ኢንፎርሜሽን ሲስተም /CRIS/ መንግስታዊ ተቋም ከሆነው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በጋራ አስለምቷል፡፡
በመሆኑም ሚንስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የዲጅታል ሬጉላቶሪ ሲስተም ትግበራ ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር
በሳይንስ ሙዚየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።