October 15, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም  27 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ)  በከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን  እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር  በጋራ  ያስለሙት የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ሚንስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት  ይፋዊ ማስጀመሪያ ሥነ  ስርዓት በዛሬው  እለት ተካሄዷል፡፡

ይህንን ሲስተም ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ  ትራንስፎርሚሽን ኢንሼትቭ  ተከትሎ የለማ ሶፍትዊር  ሲሆን  የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ስራን በማዘመንና የዘርፉን የአሰራር ስርዓት በማሳለጥ የ2030 ዲጂታል ኢኮኖሚ ግብ ለማሳካት የሚረዳ ሲስተም   እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በማስጀመሪያ  ሥነ  ስርዓቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ  ንግግር ያደረጉት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት  በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ  ትራንስፎርሚሽን ኢንሼትቭ  ወሳኝ ጉዳዮች መካከል የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ኢንፎርሜሽን ሲስተም  ማልማት አንዱ ተልእኮው ሲሆን ይህ ሲስተም  በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ያሉትን ተግዳሮቶች በመፈተሽ የስራ አካባቢውን  የተቃለጠፈ ከማድረጉም  ባሻገር  የዘርፉን  የአሰራር ስርዓት  የሚያዘምን ሲስተም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን  ዋና ዳሬክተር   ዶ/ር ኢንጂነር  መስፍን  ነገዎ በበኩላቸው  የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በአለምም ሆነ በእኛ ሀገር ደረጃ  ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት የሚያስመዘግብ እና ሰፊ  የስራ እድል የሚፈጥር  ዘርፍ ነው፡፡

ኢንዱስትሪው በተለመደው የዓሰራር ስርዓት   ብዙ ዋጋ የተከፈለበት በመሆኑ የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ኢንፎርሜሽን ሲስተም  የዘርፉን ችግሮ በመቅረፍ የተበታተነውን ዓሰራር ወደ አንድ በማምጣት  ረገድ ሚናው ከፍ ያለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

Posted in: News