
October 15, 2025
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፌደራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት እና በይርጋለም ኮንስትራክሽን በተደረገው የውል ስምምነት መሠረት ላለፉት ወራት በተከናወነው ስራ አብዛኛውን ግንባታ በማጠናቀቅ የፈደራል ፍርድ ቤቶችና መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል ፡፡
የህንፃ ግንባታው የዜጎችን በግልፅ ችሎት የመዳኘት ህገመንግስታዊ መብት ለማስከበር የሚረዳ መሆኑን እና ከዚህ ቀደም በቂ የማስቻያ ቦታዎች ባለመኖራቸዉ ሲነሱ ለነበሩ ችግሮች ምላሽ ለመስጠት፣ የፍትህ አገልግሎትን በአንድ ማዕከል ተደራሽ ለማድረግ፣ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂን በማካተት የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካት፣ በአጠቃላይ የዜጎችን ህገመንግስታዊ መብት ለማረጋገጥ የሚረዳ መሆኑ የፈደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት አቶ ተዎድሮስ ምህረት ገልጸዋል ።
ፕሮጀክቱ ግዙፍና በሀገር ውስጥ ኮንትራክተር የሚተገበር በመሆኑ በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዕድገት ማሳያና ማስቀጠያ ከመሆኑም ባሻገር የፍትህ ስርዓቱ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ይህንን ታሳቢ በማድረግ በተሻለ ብቃት የተከናወነ ነው፡፡
ግንባታው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክ/ከተማ በአዲሱ ወረዳ 9 የቦታው ስፋት 14742.99 ካሬ ሜትር፣ ህንጻው ያረፈው የቦታ ስፋት 5,926 ካ.ሜ ሆኖ ግንባታው 3 ህንፃዎችን አካቶ የያዘ ነው። በ4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የግንባታ በጀት ውል ተገብቶበታል።