May 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11 ቀን፣ 2017 ዓ.ም (ከመልሚ) 20ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ኮንፍረንስ ‹‹የማይበገር ማህበረሰብ እና ጤናማ አካባቢ፤ የሰው ኃይልን በብዛት የሚጠቀሙ የኢንቨስትመንት ፕሮግራ አካሄዶች›› በሚል መሪ ሀሳብ  በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢ አዳራሽ  ተጀምሯል ፡፡

በመርሃ-ግብሩ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና  አፈጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎና  የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ጨምሮ የተለያዩ የፌደራል መንግሰት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከ33 በላይ ሀገራት ከአፍሪካ አህጉር፣ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት፣ የተለያዩ የኮንሰትራክሽን ኢንዱስትሪው አንቀሳቃሾች በኮንፈረንሱ ተሳትፈዋል፡፡

ኮንፈረንሱን በይፋ የከፈቱት የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በኮንሰትራክሽን ኢንዱስትሪው በፈጣን የእድገት ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር መሆኗንና ለዜጎቿ ከፍተኛ የሥራ እድል እየፈጠረች ነው።

በቀጣይ ከኮንፈረንሱ በሚገኝ ልምድና ተሞክሮዎች የሀገሪቱን መሠረተ-ልማት ከፍተኛ ትኩረት ትሰራለች ብለዋል ዋና አፈጉባኤው ።

በተያያዘም ኢትዮጵያ የዜጎቿን የኑሮ ደረጃ  ለማሻሻል አካታችነትን ታሳቢ ያደረገ የልማት እንቅስቃሴዎችን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል ክቡር ዋና አፌ ጉባኤው አቶ ታገሰ ጫፎ ፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በመርሃ-ግብሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ኮንፈረንሱ በአህጉር ደረጃ የመንግድ መሠረተ-ልማትን ትግባራዊ በማድረግ ለዜጎች የሥራ እድል ፈጠራን፣ ለድህነት ቅነሳ ፣ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮችን በማጠናከር ለዘላቂ ልማት፣ የማይበገር ማህበረሰብን ለመገንባት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

ኮንፈረንሱ ለቀጣይ አራት ተከታታይ ቀናት የተለያዩ የጥናት ውጤቶች የሚቀርቡበት የፓናል ውይይቶች  እንደሚኖሩ  በመርሃ-ግብሩ ተመልክቷል፡፡

ሪፖርተር፡- ሞገስ ዓሊ
ፎቶግራፍ:_ አስመላሽ ተፈራ
                 ፌዬ ደሜ

Posted in: News