መስከረም 4, 2026
የዓለም ባንክ የመሠረተ ልማት ዘርፍ ሪጂናል ዳይሬክተር ኤሪክ ማግነስ በዘርፍ የልማት ስራዎች ዙሪያ ከሚኒስቴሩ አመራሮች ጋር መክረዋል
አዲስ አባባ፣ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና የዓለም ባንክ በዘርፉ ፕሮጀክቶች አሁናዊው ሁኔታ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና በቀጣይም በቅንጅት መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ነው የተወያዩት፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን የዓለም ባንክ በዘሪፉ የልማት ስራዎች እያበረከተ ያለውን ድጋፍ አድንቀው ይሄው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። አሁን ላይ ከተሞች ከመቸውም ጊዜ በላይ በመንግሥት ከፍተኛ ሪብርብ ምቹ
የመኖሪያ እና የመሥሪያ ማዕከላት ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተሰራ ያሉ ፕሮጀክቶች ዝርዝር አፈጻጸም እና ቀጣይ ባንኩ ድጋፍ ማድረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዋና አማካሪ አቶ ተስፋዬ ወ/ሚካኤል በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ፡፡
በዓለም ባንክ የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሪጂናል ዳይሬክተር ኤሪክ ማግነስ ባንኩ በኢትዮጵያ ትልልቅ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መጠነ ሰፊ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልጸው ይሄው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በዝርዝር በቀረበው ሰነድ መሰረት ዘሪፉን ለማገዝ ባንኩ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።