ጥር 15, 2026

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ)

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር በመሆን በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በተሻሻለው የመንግስት ግዥ ስርዓት መመሪያ ቁጥር 1073/2017 ላይ ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ባሉበት የውይይት መድረክ አካሄዷል፡፡

የህግ ማሻሻያው በአፈጻጸም ሲያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችና የህግ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ ለዘመናዊ የግዥና ንብረት ሥርዓት ትኩረት ለመስጠት፣ የስርዓቱን ግልጽነት እና ተደራሽነት ለማሳደግ፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ፣ የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎችን ተሳትፎ ለማበረታታት፣ የልማት ድርጅቶችን በአዋጁ እንዲካተቱ እና ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚረዳ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የግዥ ስርዓቱን አስመልክተው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት በነባሩ የአሰራር ስርዓት ያሉትን ችግሮች ለመፍታት አዲሱ አዋጅ ሲወጣ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን ከመንገዶች አስተዳደር ጋር በተያያዘ የሚመጡ ጥያቄዎችን ለመመለስ ፕሮጀክቱን መሰረት ያደረገ እንደ ሌሎች ልዩ መመሪያ የሚያስፈልጋቸው መስሪያ ቤቶች እንዳሉ ሁሉ ለእኛም መስሪያ ቤት ልዩ መመሪያ ያስፈልገዋል ካሉ በኋላ የግዥ ስርዓትን አስመልክቶ ለሚያጋጥሙ ችግሮች በቀጣይም አብረን የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ በበኩላቸው በግዥ ስርዓት ላይ የበላይ ሃላፊ መወሰን እና ማጽደቅ ይኖርበታል በማለት የልማት ድርጅቶች በጥራትና በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያደርግ የግዥ ስርዓት ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አያይዘውም የዶላር ለውጥን ምክንያት በማድረግ የዋጋ ማሻሻያ ማድረግ የማይቻል መሆኑን እና ጨረታ ከመውጣቱ በፊት ዋጋውን ማወቅ ሌብነትን ለመከላከል ይረዳል ብለዋል፡፡

Posted in: ዜና