የካቲት 16, 2026

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሪል ፕሮፐርቲ ግብይት፣ ግመታና ፍቃድ መሪ ስራ አስፈፃሚ አዘጋጅነት በዘርፉ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የዘርፉ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄዷል። የልምድ ልውውጥ መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የሪል ፕሮፐርቲ ግብይት፣ ግመታና ፍቃድ መሪ ስራ አስፈፃሚ አዳነ ኧግዜ(ዶ/ር) እንዳሉት ሰፊውን የሀገራችን ሀብት የሚይዘው የሪል ፕሮፐርቲ ግብይት፣ ግመታና ፍቃድ ስራዎች ሲሆን በዘርፉ የሚስተዋለውን ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት በክልሎች ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ነው። የተሰሩት ስራዎች የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድረገን መስራት እንደምገባ ገልጸዋል ። አደረጃጀት መፍጠር፣ የግብይት ስርዓቱን ማስተካከል እና ቅንጅታዊ አሰራርን መፍጠር እንደሆኑም ተናግረዋል ። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰሩ የሪል ፕሮፐርቲ ግብይትና ግመታ ስራዎችን አስመልክተው በዝግጅት እና በትግበራ ምዕራፍ  የተሰሩ ስራዎች፣ የጸደቁ የህግ ማዕቀፎች ዋና ዋና ይዘቶች፣ የተገኙ ውጤቶች፣ የነበሩ ምቹ ሁኔታዎች እና ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን የያዘ ሰነድ በዝርዝር አቅርበዋል ዶ/ር አዳነ ። በተጨማሪም በሶማሌ፣ በአፋር እና በሐረሪ ክልሎች የተሰሩ የሪል ፕሮፐርቲ ግብይትና ግመታ ስራዎች ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተካሄዷል። በውይይቱም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለሙያዎች በከተሞች ለረጅም ጊዜ በመቆት  የሚያደርጉት ክትትልና ድጋፍ ውጤታማ እንደሆነ በምርጥ ተሞክሮ ለመረዳት ተችሏል። የመረጃ አሰባሰብ ስርዓቱን የሚኒስቴር መ/ቤቱን ተሞክሮ በመውሰድና ወጥ የሆነ የሲስተም ስርዓት እንዲኖር ቢደረግ  የሚሉ ሀሳቦችን በማንሳት በዚህ ልክ የተሞክሮ ልውውጥ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል ተሳታፊዎቹ።

Posted in: ዜና