መጋቢት 6, 2026

አዳማ፣ የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት የስራ ፕሮጀክት ከዓለም ባንክ የተገኘ ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ ስራ ከመዋሉ በፊት ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚደረግባቸው 88 ከተማ ስራአስኪያጆች እና ባለሙያዎች ነው ስልጠና የተሰጠው።

መርሀ ግብሩ በይፋ ያስጀመሩት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን እንዳሉት የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ተረጂነት የሚያበረታታ ሳይሆን ዜጎች ካለባቸው ችግር በመላቀቅ የራሳቸውን ሀብት የሚፈጥሩበት ነው።

በሀገራችን የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት በ11 ከተሞች ተጀምሮ 88 ከተሞች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።ዜጎች ከተረጂነት ወጥተው ወደ አምራችነት መቀየር ትልቅ ስኬት እንደሆነም ገልጸዋል ሚኒስትር ደኤታው ።

በመድረኩ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ ፕሮጀክት ዓላማዎች እና የ3ተኛው ዙር ተጨማሪ ፋይናንስ ድጋፍ ገለጻና የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ምልመላ እና የመረጣ ሂደት ገለጻ መማድረግ ውይይት እና ማጠቃለያ ተካሄዷል

Posted in: ዜና