ህዳር 25, 2026

ኢንጂነር ሙሀመድ አብድራህማን
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14/2019 ዓ.ም (ከመልሚ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ኢንጂነር ሙሀመድ አብድራህማን የሪልእስቴት አልምዎች ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ክቡር ሚኒስትር ኢንጂነር ሙሀመድ አብድራህማን የሕዝባችን በመኖሪያ ቤት እጥረት ምክንያት የሚገጥመውን ፈተናና ስጋት በሚገባ እንረዳለን፤ ደረጃቸውን የጠበቁና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ የመመለስ ግዴታችን ነው ብለዋል።

በመንግስት ብቻ የሚገነቡ በቶች በቂ ባለመሆናቸው የግል ሴክተሩን  በፕሮግራሙ በስፋት በማሳተፍም ጭምር እየሰራን እንገኛልን በዝህም የሕዝባችንን ጥያቄ መመለስ ችለናል ብለዋል ክቡር ሚኒስትሩ።

የግሉ ዘርፍ የሚያነሳቸውን የትኛውንም ጥያቄ በቅርበት ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በዋናነት በዘርፉ የሚስተዋለውን የቴክኖሎጅ፣ የፋይናንስ፣ የአሰራር፣ የሕግ ማቅፍ እንዲሁም  የመሬት አቅርቦት ጥያቄዎች ተገብውን ምላሽ መስጠት ይገባልም ብለዋል ኢንጂነር ሙሀመድ ፡፡

በአምስት ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን ቃል ገብተናል፤ ይህንንም ቃላችንን በተግባር ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን ስሉ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።

የማህበሩ የስራ ሀላፊዎች ከአሰራር፣ ከህግ ማእቀፎች፣ ከፋይናንስ አማራጮች እና መሰል ጉዳዮች ጋር አሉብን ያሉትን ጥያቄዎች በማቅረብ መንግስት መፍትሔ እንድሰጥ ጠይቀዋል።

ዘርፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚመራበት የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ምክንያት በሪል እስቴት አልሚውና በገዥው መካከል የነበረው ግንኙነት ተአማኒነት የጎደለው ነበር  መንግስት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል አዋጅ መውጣቱን በመግለጽ አዋጁ የሚመራባቸው ፕሮግራሞች ተቀርፀው አዋጁ ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የአልሚዎች አቅም ጎልብቶ፣ ገዥው መብቱ ተከብሮ በሻጭና ገዥ መካከል መተማመንን የሚፈጥር መልካም ግንኙነት ይፈጥራል ብለዋል የማህበሩ የስራ ሀላፊዎች፡

Posted in: ዜና