ታህሳስ 29, 2025

አዳማ፣ ታህሳስ 14 ቀን፣ 2018 ዓ.ም(ከመልሚ)
በሚኒስቴር መ/ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ በዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዙሪያ ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

በከተማና መሠተረተ ልማት ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበራ አመንታ በስልጠናው ላይ እንደተናገሩት ሁሉንም የአሠራር ሥርዓቶችን ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ የተናበበ ዕቅድ ለማዘጋጀት ስልጠናው ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናው የተሠጠው ከዘርፉ ለተውጣጡ የዕቀድና በጀት ፕሮግራም አመራሮችና ባለሙያዎች ዕቅድንና በጀትን አጣጥመው የሚያቅዷቸው ዕቅዶች ለውጡታማ ስራ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አቶ አበራ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የፕላን ልማት ሚ/ር የፕላን ኢነቭስትሜንት ዴስክ ኃላፊ አቶ ከተማ ፉፋ ባቀረቡት ሰነድ እንደተናገሩት ዕቅድ ውስን ሀብትን ለታለመለት ዓላማ በታማኝነትና በተጠያቂነት ማከናወን እንደሚገባ ጠቅሰው ለዕቅድ አፈጻጸም ውጤታማነት ነባራዊ አቅምን እና ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ዕቅድን ከሠው ኃይል፣ ከፕሮግራምና ፋይናንስ ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ ሠልጣኞች ከፍተኛ ትኩረት ሊሠጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ከዕቅድ እስከ ግብረ-መልስ ድረስ ወጥነት ያለው የዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ሊተገበር እንደሚገባና አሳሳች ሪፖርቶች መወገድ እንዳለባቸው እና ጥራቱን የጠበቀ ሪፖርትና ውጤታማ የሆነ የእቅድ አዘገጃጀት እንዴት እንደሚዘጋጅ በቂ ግንዛቤ ማገኘታቸውን ሠልጣኞች በውይይት መድረኩ ተናግረዋል፡፡

በሚኒስቴር መ/ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ዘነበ ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ስጥተዋል። እንደአቅጣጫ እና አሰራር የሚወርዱ አዳዲስ አሠራሮችን በመረዳዳትና በመተጋገዝ በየደረጃው የምንገኝ አመራርና ባለሙያዎች ተቀናጅተን ልንሠራ ይገባናል ብለዋል፡፡

Posted in: ዜና