
ጥቅምት 15, 2025
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29/2018 ዓ.ም (ከመልሚ)
የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሠራተኞች በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር በጉምሩክ ኮሚሽን የተዘጋጀውን የቴክኖሎጂ ዐውደ-ርዕይ በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ሂደት ወደ ዘመናዊ ታክስ አስተዳደር ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ቀጣይ የቴክኖሎጂ ሥርዓቶች፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኤሌክትሮኒክ የአንድ መስኮት አገልግሎት ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ሥራ አመራር ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ የሰው ኃብት ልማት ልህቀት ሥርዓት፣ የጉምሩክ የገቢ አፈጻጸም መከታተያ ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ የመንገደኞች ስጋት ሥራ አመራር ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ቻትቦት፣ የጉምሩክ አስተላላፊና የጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ዘመናዊ የድንበር ቁጥጥር ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኤሌክትሮኒክ የጭነት መከታተያ ሥርዓትን የተመለከቱ በቴክኖሎጂ የተደገፉ የአሠራር ሥርዓቶች የዓውደ-ርዕዩ አካል ነበሩ፡፡
በቴክኖሎጂ የተደገፈው አሠራር በሁሉም ረገድ የሚታዩ መጉላላቶችን ለመቀነስ፤ ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና ህጋዊ ሥርዓትን ለማስፈን ሁነኛ መፍትሄ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር በክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዓሊ (ዶ/ር) የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም መመረቁ ይታወሳል፡፡