ጥር 15, 2026
አዳማ፣ ታህሳስ 25፣ 2018 ዓ.ም(ከመልሚ)
ሁሉም ክልል፣ የአድስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የዘርፉ የህዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ አካላት የጋራ ፎረም የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል ፡፡
የውይይት መድረኩ በዋናነት ትኩረት ያደረገው የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎረም እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢንሸቲቭ ላይ ነው፡፡
የፎረሙን መድረክ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አባድር ፋሪስ እንደተናገሩት በሚኒሰቴር መስሪያ ቤቱ የተቀረጹ አጠቃላይ አዳዲስ የህግ ማዕቀፎች በሚዲያና በህዝብ ግንኙነት መዋቅር ወደ ህብረተሰቡ መረጃን በግልጽነት ተደራሽ ለማድረግ መድረኩ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
አቶ አባድር አክለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያካናውናቸውን ተግባራትን ከፌደራል እስከ ታችኛው መዋቅር እየተመዘገቡ የሚገኙ ለውጦችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ የሚቻለው በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አካላት በመሆኑ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከሁሉም የሚዲያ አካላት ጋር ተቀራቦ እየሠራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈጻሚ አቶ አዱኛ አለሙ የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም በምመለከት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ሪፎርሙ አካታች፣ ከአድሎ የጸዳ፣ ለተገልጋይ ደንበኛ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎትን በተጠያቂነት ለመስጠት እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር ለተገልጋይ ደንበኞች ለማቅረብ ሚኒስቴር መ/ቤቱ የሪፎሪሙን የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን እየሰራ እንደሆ ገልጸዋል ፡፡
በሀገራችን የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ስርዓት ከተመሰረተ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ ቢሆንም በሚፈለገዉ ደረጃ ዜጎች የሚፈልጉትን መንግስታዊ አገልግሎት በማቅረብ፣ ፍትሃዊ አስተዳደርን በማስፈን፣ ነጻና ገለልተኛ ከመሆን አንጻር ዘርፉ አሁን ያለበት ደረጃ አሳሳቢና ከዚህ ትዉልድ አስቸኳይ ምላሽ የሚፈልግ በመሆኑ በሁለንተናዊ መልኩ ችግር ፈችና ዉጤታማ የሆኑ ነጻ፣ ገለልተኛና ብቁ ተቋማትን በመፍጠር ለሀገረ መንግስት ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት አዲስ የለዉጥ ማዕቀፍ ለመተግበር እንደሀገር የሪፎርም ስራ መጀመሩን ተናግረዋል አቶ አዱኛ፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አማካሪ በቀለ ንጉሴ(ዶ/ር) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ትራንስፎርማሽኝ ኢንሽቲቭን አስመልክተው ባቀረቡት ሰነድ ዘርፉ በመንግስት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መምጣቱን ጠቅሰው ይሁንና በርካታ ተግዳሮቶች የተደቀኑበትና ከውጭ ሀገር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቁ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ተክቶ ለመስራት በሰፊው እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አካላት ስለ መንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም እንዲሁም ስለ ኮንስትራክሽን እንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽኝ ኢኒሼቲቭ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋሉ ብዥታዎችን ግልጽ በሆነ መንገድ በሚጠቀሙባቸው የሚዲያ አግባቦች ለዜጋው በተገቢው መንገድ መረጃዎች ማድረስ እደሚገባቸው የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ኢትዮጵያ በደቻ አስገንዝበዋል፡፡
ስለ ሪፎርሙ እንዲሁም ስለ ኢኒሼቲቭ ለህ/ሰቡ መረጃ ማቅረብና ግልጽነት ማስፋፋት፣ ህዝብን ማስተማርና ማሳወቅ ወቅታዊ መረጃ መስጠት፣ በተሳሳተ አዉድ ሲተረጎም ከትክክለኛ ምንጭ መረጃ በመዉሰድ መረጃ ተደራሽ የማድረግ፣ ያልተረጋገጠ መረጃ መቆጣጠር፣ አስተያየትና ዜና መለየት፣ የሙያ ስነምግባር መከተል ፣ በአጠቃላይ የተደራጀ፣ ወቅታዊ፣ ታማኝነትና ግልጽነት ያለዉ መረጃ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረግ እና ተጠያቂነትን ማስፈን ይጠበቅብናል ብለዋል አቶ ኢትዮጵያ ።
በመጨረሻም የቀረቡትን ሀገራዊ ጉዳዮች ተግባራዊ ለማድረግ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት አካላት መረጃን ለህበረተሰቡ በተገቢው መንገድ ማድረስ እንደሚገባቸው የጋራ አረዳድ ላይ ተደርሷል፡፡