መጋቢት 19, 2026
አዲስ አበባ ፣መጋቢት 3 ቀን፣2018 ዓ.ም (ከ.መ.ል.ሚ) ለዜጎች የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ነጻ ገለልተኛ እና ብዝሃነት ያካተተ ሲቪል ሰርቫንት መገንባት እንደሚያስፈልግ ተግልጸ፡፡
ይህ የተገለጸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመንግሰት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም በተጠኑ ሁለት ሰነዶች ዙሪያ በተሠጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ነው፡፡
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን እንደተናገሩት ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ ብሎም የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ነጻ ገለልተኛ እና ብዝሃነት ያካተተ ሲቪል ሰርቫንት መገንባት እንደሚያስፈልግ ለተቋሙ አመራሮችና እና ሠራተኞች አብራርተዋል፡፡
የጥናቱን ያቀረቡት አቶ ባህሩ አሽኔ በተሿሚዎችና በመንግሥት ሠራተኞች መካከል ስለሚኖረው ግልጽ የሥራ ክፍፍልና መስተጋብር አስመልክቶ በሪፎርሙ መተኮር ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዘር አቅርበዋል፡፡
አቶ ባህሩ አክለውም ነጻና ገለልተኛ ሲባል የአፈጻጸም ውጤታማነትን፣ ውድድርን፣ ሙያዊ ብቃትንና ችሎታን መሠረት ያደረገ የሥራ ስምሪትን፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጡ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የሠራተኞች የቅሬታ እንዲሁም የዲስፕሊን መፍቻ አደረጃጀቶችና አሠራሮችን በማጠናከር ፍትሐዊ አሠራርን መከተል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ለተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች ስለ ብዝኃነትና አካታችነት ምንነት እና አተገባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ያቀረቡት አቶ ቴዎድሮስ ሰመረ እንደተናገሩት የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ እና ነባር አሠራሮችን በጥልቀት በመገምገም የብሔር፣ የጾታ፣ የዕድሜ እና የአካል ጉዳተኝነትን ከግምት ያስገባ ዝርዝር የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀትና መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
አጠቃላይ የህግ ማዕቀፎች ሲወጡና ሲተገበሩ የዘርፉ ስራዎች ውሳኔዎች እና የሚሰጡ መረጃዎች ብዝኃነትንና አካታችነትን መሠረት በማድረግ ለማከናወን የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች፣ ዕቅዶች፣ ማንዋሎችን በማዘጋጀት ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ ባቀረቡት የጥናት ሰነድ ገልጸዋል፡፡
ሁለቱም ሰነዶች ከቀረቡ በኋላ ከቤቱ በርካታ አስተያየቶች ተነስተዋል ፡፡ ሪፎርሙ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ሲገባ ነባሩን አሠራር በመቀየር ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊ፣ ሁሉን አቀፍ፣ መንግስታት ቢቀያየሩም እንኳ በዘላቂነት የሚኖረው የከተማ ነዋሪዎችን በእኩልነት ሊያገለግል የሚችል ሪፎርም እየተሰራ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል ፡