ጥቅምት 27, 2025
ሐረር፣ ጥቅምት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም (ከ.መ.ል.ሚ) የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካማ ዜጎች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች አስመርቆ ለተጠቃሚዎች አስረክቧል፡፡
በሐረር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት በአማር ኑር ወረዳ ሴዳት አካባቢ ለሚገኙ ለስምንት አባውራዎች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አቅመ ደካማና እጅግ በጣም በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ዜጎች አስፈላጊ የሚባሉ ቁሳቁሶችና መሠረተ-ልማት የተሟላላቸው ቤቶችን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ቤቶቹን አስገንብቶ በማስመረቅ ለጠጠቃሚ ዜጎች የቁልፍ ርክክብ ተካሂዷል፡፡
መኖሪያ ቤቶቹ በ20 ሚሊዮን ብር ወጭ በሶስት ወራት ውስጥ ተገንብተው ለጠጠቃሚዎች ርክክብ እንደተደረገና ሁሉም ቤቶቹ ባለአንድ ምኝታ ሲሆኑ በውስጣቸው አስፈላጊ ለኑሮ ምቹና የከተሜነት መገለጫ የሆኑ ሁለት ብሎኮች ተጠናቀው ለተጠቃሚ ዜጎቹ ርክክብ ሲደረግ አቅመ ደካማ አባቶችና እናቶች መንግስት ላደረገላቸው ድጋፍ አመሰግንዋል፡፡
በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሔለን ደበበ መንግስት ላለፉት ሰባት ዓመታት የህብረተሰቡን ኑሮ ለማማቻቸት ዜጋ ተኮር ስራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ ጠቅሰው በተለይ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከባለድርሻ አካላት ጋር በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡
ዜጎች ከተርጅነት ወጥተው የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ መንግሰት ከፍተኛ ጠረት እያደረገ እንደሚገኝ የጠቀሱት ሚ/ዴኤታዋ የከተማ ነዋሪዎች በንጹህ አካባቢ፣ የተመቻቸ ኑሮ እንዲፈጠርላቸው በርካታ ሰው ተኮር ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡
የሀረር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት በምክትል ር/መስተዳድር ማዕረግ የከተማና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ እንደተናገሩት ለሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞን ለማረጋገጥ በዝቅተና ኑሮ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅ ተናግረው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ሌሎች ባለድርሻ አካት ለሰሩት መልካም ስራ አመስግነዋል፡፡
በመጨረሻም የመኖሪያ ቤት ቁልፉን ለተጠቃሚዎች ያስረከቡት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚ/ዲኤታ ክብርት ወ/ሮ ሄለን ደበበ እና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ ናቸው።