ሚያዝያ 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8/2017 ዓ.ም፣ (ከመልሚ)

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ይህን የተናገሩት በዛሬው ዕለት በ2017 በጀት ዓመት በተያዙ ሀገራዊና ተቋማዊ ዕቅዶች አፈጻጸም ላይ በካቢኔ እና በማኔጅመንት የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ መካከለኛ አመራሮችና አጠቃላይ ሠራተኞች በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተገመገመውን ሠነድ ያቀረቡ ሲሆን በአወያይነትም የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ክቡር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ተገኝተውበታል፡፡

እንደክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ገለጻ የቀረበው ሠነድ በስድስት ክፍሎች የተዘጋጀ ሆኖ በዋናነት ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያና ለኢትዮጵያ ያለው እንደምታ፤ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ እና ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን ማረጋገጥ፤ በመንግስት አገልግሎትና የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻይ ስራዎች ላይ የታዩ ለውጦች፤ ዘላቂ ልማት፣ ማህበራዊ አካታችነት እና ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት፤ አስቻይ ሁኔታ ለዘላቂ ልማት፣ ሠላም፣ ዲፕሎማሲ እና ትብብር በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በተሰሩ ስራዎች የተመዘገቡ ሀገራዊ ውጤቶችን ከዓለም አቀፉና ከአህጉር አቀፍ ሀገራት ጋር በማነጻጸር በአሀዝ የተደገፈ ዝርዝር ማብራሪያን ያቀረቡ ሲሆን ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይና አስቻይ ሁኔታዎች ላይም የተብራራ መረጃን ሰጥተዋል፡፡

ገለጻውን ተከትሎ በሰነዱ ላይ በቀረቡት መረጃዎች መነሻነት ተያያዥነት ያላቸው ዓለም አቀፋዊ፣ ሀገራዊ እና ተቋማዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተወያዮቹ ቀርበው ከመድረክ በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትሯ በሰጡት የማጠቃለያ አስተያየት የሀገርን ህልውና ለማስከበር የምንከፍለውን መስዋዕትነት ያህል ሀገርን ለማጽናትና ከተረጂነት የተላቀቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር ጊዜው የሚጠይቀውን የለውጥ እርምጃ ዕውን በማድረግ በልማቱ መስክ ሀገርን ማጽናት አሁን ያለው ትውልድ ሀገራዊ ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ በደም ያስከበርናትን ሀገር በላባችን ማጽናት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ስለሺ ዘገዬ
የካሜራ ባለሙያ፡- አስመላሽ ተፈራ

Posted in: ዜና