የካቲት 24, 2026
አዳማ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) ክበርት ሚኒስትሯ ይህንን ያሉት የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የዘርፉ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ከኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፓርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት፣ የሚኒስቴሩ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች፣ እንዲሁም የክልልና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የተቋሙ ሴክተር ጉባኤ ላይ ነው፡፡
በከተማ ልማት ዘርፍ በአጠቃላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤት እጅግ አስደማሚ እንደሆነ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፓርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በክልሎች ባደረጉት ክትትልና ድጋፍ የክልል እና የከተማ መስተዳድር የስራ ሃላፊዎች ለዚህ ውጤት መብቃት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በጉባኤ በቀረበው የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ግማሽ አመት የዘርፉ አፈጻጸም ከተሳታፊዎች በርካታ ሀሳቦች የተነሡ ስሆን ክብርት ሚኒስትር በማጠቃለያቸው በከተሞች እና በክልል ደረጃ የካዳስተር ስርዓት በመዘርጋት በውጤቱም እና በአገልግሎት አሰጣቱ የረካ ማህበረሰብ በፍጠር ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገብ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
በቀጣይ በከተሞች ገቢ፣ በቤት ልማትእና የቤቶች መረጃ አስተዳደር፣ በከተሞች የአርንጓዴ ሽፋን፣ የገጠር ቀበሌ የልማት ማዕከላትን በማስፋፋት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን፣ ከተሞች በፕላን እንዲመሩ እንዲሁም የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮጀክቶች እና በአጠቃለይ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢንሼቲቭ የኛም በመሆኑ ሁሌም ከአመራር እስከ ፈጻሚ ያለው አካል ለዕቅዱ መሳካት ተግቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል ፡፡