ጥቅምት 10, 2025

አዲስ አበባ፣መስከረም 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም (ከ.መ.ል.ሚ)
የመሠረተ-ልማት ክላስተር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የየባለድርሻ አካላት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓምት ዕቅዳቸውን ተወያይተው አጸድቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በመሠረተ-ልማት ክላስተር የተደራጁ ተቋማት ከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር በሰብሳቢነት፣ ትራንሰፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን፣ ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ኢትዮ-ቴሌኮም፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የዘርፉ ማህበራት ተወካዮች ናቸው፡፡

የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ለአምራች ኢንዱስትሪው እድገትና ተወዳዳሪነት ተግዳሮትና ማነቆ የሆኑ የመሠረተ ልማት ችግሮችን በመለየት ስትራቴጂካዊ በሆነ አካሄድ እና በቅንጅታዊ አሰራር መፍትሄዎችን በመስጠት የማምረት አቅም አጠቃቀምን ማሻሻል እንዲሁም በጅምር ያለውን የኢንዱስትሪያል ማህበረሰብ ግንባታ ለማጠናከር የበኩልን ሚና እንዲወጣ ታስቦ የታቀደ እቅድ እንደሆነ በቀረበው እቅድ ላይ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በ2014 ዓ.ም እንደተመሠረተ የሚነገርለት ዋና ዓላማው የአምራች ኢንዱስትሪው የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ባቀደው ዕቅድ መሠረት ከላይኛው እስከ ታችኛው መዋቅር በመናበብ፣ በመቀናጀት እና በመተባበር ችግሮችን በፍጥነት በመፍታት የሀገሪቱን የውጭ ንግድ በብዛትና በጥራት ከፍ እንዲል ስራዎችን ማከናወን እንደሆነ በመድረኩ ተብራርቷል፡፡

Posted in: ዜና