ሰኔ 4, 2025

ቢሸፍቱ፣ ግንቦት 22 ቀን፣ 2017 ዓ.ም (ከመልሚ)፡- በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የመሠረተ-ልማት ዘርፍ የ2017 ዕቅድ አፈጻጸምንና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ የየተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በቢሸፍቱ ከተማ የምክር መድረክ አካሂደዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የተሳተፉት ከተጠሪ ተቋማት የኢትዮጵያ መንገዶች አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እንስትቲዩት ሲሆኑ፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ደግሞ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ፣ የተቀናጀ የመሰረተ-ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ፣ የኮንስትራክሽን መሠረተ-ልማት መሪ ስራ እና የገጠር መንገድ ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የእረስበርስ ልምድና ተሞክሮዎቻቸውን አቅርበው ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የከተማና መሠረተ-ልማት ሚ/ ዴኤታ ክቡር አቶ የትምጌታ አስራት እንደተናገሩት ሁሉም ተሳታፊ አመራሮች በያዝነው በጅት ዓመት ያከናወኗቸውን መልካም ተሞክሮዎችን እና የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክተው የጋራ አረዳድ በመፍጠር የሀገሪቱን መሠረተ-ልማቶች ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ እነደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ዘርፉ ለሀገራችን ኢኮኖሚ የሚያበረክተው ድርሻ እጅግ የላቀ ነው ያሉት ሚ/ ዴኤታው ሁሉም የስራ ክፍሎች በመናበብና በመቀናጀት፣ አንዱ ለሌላው ስራ ክፍል እንቅፋት ከመሆን ይልቅ እርስ በረስ ተደጋግፎ የመረጃ ልውጥን በቅንነትና በታማኝነት በማቅረብ ትክክለኛ ለሆነ ተቋማዊ ግንባታ መረባረብ አቶ የትምጌታ አሳስበዋል፡፡

በየደረጃው ከሚገኝ ባለሙያ እስከ አመራር ድረስ ስራና ውጤትን መሠረት ያደረገ ጠንካራ የግምገማና ክትትል ሥርዓት መዘርጋቱን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል ፡፡

መድረኩ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ በመርሃ-ግብሩ ተመልክቷል

Posted in: ዜና