ጥር 1, 2026

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ)

የመንግስ አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም የመንግስት የአገልግሎት እና የአሠራር ቅልጥፍና ለማምጣት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ዘመኑ ከሚያራምደው የአስተዳደር ሳይንስ ውጤት መሠረት አገልግሎትን ለዜጎች ለማቅረብ የሠራተኛው የእውቀት፣ የክህሎት፣ የአስተሳሰብ፣ የሞራል፣ እና የባህሪ ክፍተቶች ለማስተካከል የሚሰራ ሪፎርም ነው፡፡

የተቀናጀ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ማካሄድ በማስፈለጉ በ2ኛ ዙር ሪፎርም ተግባራዊ ለማድረግ የዝግጅት ምዕራፍ ከሚያደርጉ ተቋማት አንዱ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በመሆኑ ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ እየሠራ ይገኛል፡፡

የዝግጅት ምእራፍ ሳምንታዊ የሪፎርሙ ስራዎችን በማስመልከት በየንዑሳን ኮሚቴዎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እና ለሪፎርሙ መሳካት የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ጉዳዮች፣ ተግዳሮቶች መፍትሔ እንዲበጅላቸው በሪፓርቱ ተመልክቷል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት ሪፓርቶች መሠረት ዝርዝር ውይይት የተካሄደ ሲሆን ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋቋመው ኮሚቴ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በተቀናጀ መንገድ መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል ፡፡

የምንሰራቸው የሪፎርም ስራዎች በጥራት እና በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ መጠናቀቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

Posted in: ዜና