ታህሳስ 12, 2025
አዲስ አበባ፣ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ)
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ እንደ ሀገር አቀፍ ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ “ትውልድን በስነ- ምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር ” በሚል መሪ ቃል የጸረ-ሙስና ቀን እየተከበረ ነው፡፡
ትውልድን በመልካም ስነ-ምግባር የሚገነቡ እና በተቋማት የአሰራር ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን የሚያስችል የንቅናቄ ስራዎችን በመፍጠር በአሉ እየተከበረ ያለው፡፡
ፕሮግራሙን በንግግር ያስጀመሩት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት እንደ አለም አቀፍና እንደ ሀገር “ትውልድን በስነ- ምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር ” በሚል መሪቃል እየተከበረ ያለው የጸረ-ሙስና ቀን ስናከብር ስለሌላ ሰው ሳይሆን ስለራሳችን፣ ስለሌላ ተቋማት ሳይሆን ስለራሳችን ተቋም በማሰብና ለሙስና መከላከል ትልቅ ቦታ ከመስጠት ጎን ለጎን ትውልድን በሥነ ምግባር መቅረጽ ያስፈልጋል ብለዋል።
የከተማና መሠረተ ልማት ዘርፍ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ በመሆኑ ሁሉም ከህሊና ጋር የሚያስታርቅ፣ እራስን የሚያስከብር እና ለትውልድ የሚሻገር ስራ መስራት ይኖርብናል በማለት በአጽንኦት ተናግረዋል።
የፌደራል ሥነ ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው የዛሬው የጸረ-ሙስና ቀን ግንዛቤ የሚፈጠርበት እና የተቋሙ የበላይ አመራሮች ሀብታቸውን አስመዝግበው ለኮሚሽኑ የሚያስረክቡበት ነው።
ከሙስና መንስኤዎች መካከል የአመለካከት ብልሹነት፣ የማህበራዊ እሴቶች መሸርሸር እና በየተቋማቱ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት አለመፍጠር እና መሰል ጉዳዮች ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሙስና አስከፊነትን በማስተማር፣ በማስገንዘብ በማስጠንቀቅ፣ በእያንዳዱ ተግባራት በማካተት፣ ሀብትን ማስመዝገብ፣ አሰራርን በማዘመን፣ በማጋለጠ፣ ሀብትን በማስመለሰ ሙስናን መከላከል እንደምቻል አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል።
በመድረኩ ሁሉም የዘርፍ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሀብታቸውን አስመዝግበው ለኮሚሽኑ በማስረከብና በቀረቡት የመነሻ የውይይት ሰነዶች ውይይት በማድረግ የእለቱ መርሀ ግብር ተጠናቋል