የካቲት 24, 2026

አዳማ፣ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልማ)

በመድረኩ የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና አባላት፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች የክልልና የከተማ አስተዳደር የሥራ ሀላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የተቋሙ ሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

ጉባኤውን በንግግር ያስጀመሩት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት ሚኒስቴር መስሪያ ቤ/ቱ የሀገራችንን ራዕይ እውን ለማድረግ እና የከተሞቻችን ብልጽግና ሁለንተናዊ ለውጥ ለማረጋገጥ የሚጫወተው ሚና ጉልህ እንደሆነ በከተሞች በተሰሩት የልማት ስራዎች በተጨባጭ እየታየ ነው፡፡

በተለይም አሁን በያዝነው የአስር አመት የልማት እቅድ ከተሞች የኢንዱስትሪ መዳረሻ እና የኢኮኖሚ ማዕከል እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር በከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱንም ገልጸዋል ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ፡፡

የከተሜነት ፍላጎትና ፍልሰት፣ የህዝቡም ቁጥር ማደግ በዕውቀትና ጥበብ ለያዘው መልካም ዕድል፣ በአግባቡ ካልተመራ ደግሞ ትልቅ አደጋ በመሆኑም መንግሥት ይህንን እውነታ በውል ተገንዝቦ ለከተሞች ዕድገትና መስፋፋት፣ለዜጎችም ህይወት ማማርና መቃናት በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደምገኝ ተናግረዋል ፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ዋና ዋና ስራዎችን የተመለከተ የዘርፍ መካከለኛ ዘመን የልማትና የኢንቨስትመንት ዕቅድ መሰረት በማድረግ የ2018 በጀት ዓመት የሴክተሩ ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን ይህን ተከትሎም ከሚመለከታቸው የክልልና ከተማ አስተዳደሮች የዘርፍ አደረጃጀቶች ጋር በዋና ዋና የትኩረት መስኮች ዙሪያ ዕቅዱን በጋራ ለመፈጸም ላለፈው ግማሽ አመት መሠራቱን ገልጸው በዕቅድ የተያዙ ስራዎችን በፍጥነትና በጥራት ለማከናወን እንዲቻል በየሩብ ዓመቱ የአፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ የሚገመገምበት የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱን እና ውጤታማ መሆኑንም ገልጸዋል ሚኒስትሯ ።

የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዘርፉ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ዘነበ አቅርበው ውይይት እየተደረገ ነው።

Posted in: ዜና