
ነሐሴ 4, 2025
አድስ አበባ: ሐምሌ 24/2017 ዓ. ም (ከመልሚ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖር እንዲችል ምቹ አካባቢ የሚፈጥር መሆኑን ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ቤተሰብ በሸገር ከተማ በሰበታ ክላስተር በፉሪ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው በአቢቹ ት/ቤት በአንድ ጀንበር የ700 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ባስጀመሩበት ወቅት ተናግረዋል ።
በሸገር ከተማ በሰበታ ክላስተር በፉሪ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው በአቢቹ ት/ቤት በአንድ ጀንበር የ700 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ላይ ተተገኝተው የአረንጓዴ ዐሻራቸውን ያኖሩት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት አረንጓዴ ዐሻራን ማኖር ብቻ ሳይሆኖ የተፈጥሮ ሚዛንን መጠበቅና መንከባከብ ያስፈልጋል ብለዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሰው ልጅ ንጹህ አየርና ውሃ እንዲያገኝ እንዲሁም ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖር እንዲችል የሚያደርግ በመሆኑም አጠናክረን ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል ክብርት ሚኒስትር ።
አረንጓዴ አሻራ የተፈጥሮ ሚዛንን በመጠበቅ የብልፅግና ጉዞአችንን የምናሳካበት እና ከተሞቻችንን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ ፣ ለኑሮ እና ለስራ ተስማም እንዲሆኑ ጉልህ ሚና ይጫወታል።
ዘንድሮ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻ የተገኙትን ውጤቶች ከፍ ማድረግ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ችግኞችን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መ/ቤት፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አመራር እና አጠቃላ ሠራተኛውን በሸገር ከተማ በሰበታ ክላስተር በፉሪ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው በአቢቹ ት/ቤት በአንድ ጀንበር የ700 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ አከናውነዋል።