መጋቢት 30, 2026
በቤት ልማት ግብአት ጥናትና ምርምር እንዲሁም የማማከር ስራ ላይ ከተሰማራው መከንዚ ከተባለ የብሪትሽ ድርጅት ጋር ውይይት አካሂዷል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የጉባ ቃልኪዳን ከሆኑት አንዱና ዋነኛዉ 1.5 ሚሊየን ቤቶችን በመገንባት የሕብረተሰቡን የቤት ጥያቀ ለመመለስ እንድሰራ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህ አቅድ ተግባራዊ እንዲሆን የቤት ልማት ፓሊስ ከማውጣት ጀምሮ በርካታ ስራዎችን እሰራ ነው ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለቤት ልማት ዕቅድ ውጤታማነት የጸደቀው ፖሊሲ፣ ፕሮግራሞች እና የቴክኖሎጂ አማራጮች መሰረት በማድረግ ምን ያህል ዋና ዋና የግባታ ግባዓት ያስፈልጋሉ የሚልና ምን ያህሉን በሀገር ውስጥ መተካት ይቻላል ከሀገር ውጭስ ምን ያህል ያስፈልጋል፤ የሚለውና ምን አይነት ምቹ ሁኔታዎች እና ተግዳሮቶች አሉ በሚል ሰፊ ጥናት እያደረገ ሲሆን ይሄንኑ ሊያጠናክር የሚችል ውይይት ነው የተካሄደው ፡፡
በቤት ልማት ግብአት ጥናትና ምርምር እና የማማከር ስራ ላይ የተሰማራው መከንዚ የግንባታ ግብዓት አቅርቦትና ስርጭት አስመልክቶ በአምስት ዓመት ውስጥና ከአምስት ዓመት በኃላ በሀገር ውስጥ የሚሸፈኑና እና ከውጭ የሚገቡ የግንባታ ግብዓት እንዲሁም ምን ያህልስ የግንባታ ግብዓት ያስፈልጋል የሚለውን መለየት የሚያስችል ያጠናውን ዝርዝር ጥናት ለውይይት ቀርቧል፡፡
ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሄለን ደበበ በውይይት መድረኩ እንዳሉት የግንባታ ግብአቶችንና የግንባታ ቴክኒዎሎጂ አቅርቦትን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን ጋር ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጥናት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
የተጀመረውን የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢኒሼቲቭ እና የጉባ ቃልክዳን ሰነድ አካል የሆነውን የ1.5 ሚልዮን ቤት ልማት ለማሳካት ሰፊ እርብርብ ከተደረገ እንደሆነ ጠቅሰው ነገር ግን በቀጣይ ሰፋፊ ውይይቶች እንደሚደረጉ እና አሁን የቀረቡት ጥናቶች ዳብረው ወደ ስራ እንደሚቀየሩ ተናግረዋል።