የካቲት 24, 2026

አዳማ፣ የካቲት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም (ከ.መ.ል.ሚ) የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ዘርፍ ተኮር የፀረ-ሙስና ትግል በተለይ ከዘርፉ የክልል የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተቋሙና የተጠሪ ተቋማት የከፍተኛ አመራሮች በውሳኔ አሰጣጥና በጥቅም ግጭት ዙሪያ በሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሺን የተዘጋጀ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በመላው ሀገሪቱ በተለይ በውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሚገኙ አመራሮች ስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የጥቅም ግጭትን በማስወገድ በመልካም ሥነምግባር የታነጸ አመራር ለመፍጠር ስልጠናው ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው በመድረኩ ተገልጿል።

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንደተናገሩት ዘርፉ በከተሞች ከሚሰጠው አገልግሎት ጋር ተያይዞ የጥቅም ግጭትን አስወግዶ በየደረጃው የሚገኝ አመራር ራሱን ከሌብነት በማጽዳት ሁሉንም ዜጋ በፍትሐዊነትና በተጠያቂነት ማገልገል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም በሥነ-ምግባርና ቅሬታ አቀራረብ፣ በጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ዜጎች ከብልሹ አሰራር ራሳቸውን ነጻ አድረገው በከተሞች የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችም ትኩረት ሰጥተው በመስራት ለሀገርና ለወገን በሚጠቅም ተግባር ላይ መሠማራት እንደሚገባ ጠቁመው የከተማ ነዋሪዎችን በቅንነትና በታማኝነት ልናገለግል ይገባል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፐብልክ ሰርቪስ ዩነቨርሰቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዮሐንስ እና ከጅማ ዩኒቨርሰቲ የሱፍ ኢብራሂም(ዶ/ር) በጥቅም ግጭትና በውሳኔ አሰጣጥ ዙሪያ ለአመራሮች ስልጠና ሰጥተዋል።

በኮንሰትራክሽን ኢንዱስትሪው፣ በመሬት ዘርፍ፣ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና በመኖሪያ ቤቶች አቅርቦት ረገድ አገልግሎት ስንሰጥ የጥቅም ግጭትን በማሰወገድ በውሳኔ አሰጣጥ የህዝብን ጥቅም ማስቀደም ወይም አደራን በመወጣት እንደ አመራር የሥነ-ምግባር መርሆችን በመጠበቅ ለዜጎች ተገቢውን አገልግሎት በፍትሃዊነት መሠጥት እንደምገባል በስልጠናው ተገልጿል።

የጥቅም የግጭትን ለመከላከል ሁሉም አመራር የተሟላ ስብዕና፣ ያለአድልኦ ማገልገል፣ ተጠያቂነትን ማስፈን፣ ታማኝነት፣ ዜጎችን ማክበር፣ ፈጣን ምላሽ መስጠት እና ሌሎች በጎ ተግባራትን ማካናወን እንደምገባም ተነስቷል በስልጠናው ፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ አመራሩ ሀብቱን ማስመዝገብ፣ ለዘጎች ድጋፍ ማድረግ፣ ማስተማር መከላከል አስተዳደራዊ ርምጃ መውሰድና ሌሎች መከላከያ መንገዶችን ተጠቅመው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተገልጿል፡፡

የፌደራል ሥነ-ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ፍቃዱ ሶቦቃ በከተሞች በየደረጃው የሚገኝ አመራር በተሰጠው ስልጠና መሠረት ኃላፊነታቸውን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

Posted in: ዜና