የካቲት 16, 2026

የከተሞችን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ለመፍታት መፍትሔው ዲጅታል አሠራርን ተግባራዊ ማድረግ ነው ሲሉ የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን ገለጸዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት በአዳማ ከተማ ለሁሉም ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስታንዳርድ፣ በመሬትና ካዳስተር፣ በማዘጋጃ ቤታዊ ገቢና የከተማ ፕላን ዙሪያ በተጠው ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡ የሀገራችን የከተማ ነዋሪዎች መሠረታዊ የመልካም አስተዳደር ችግር መነሻ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስታንዳርድ፣ በመሬትና ካዳስተር፣ በማዘጋጃ ቤታዊ ገቢና የከተማ ፕላንን ዙሪያ ዘመኑ የሚጠይቀውን የድጅታል አሠራር ተግባራዊ ባለማድረግ ነው ያሉት ሚኒስቴር ዴኤታው ይህንን መሠረታዊ ችግር ለመቅረፍ ያላቸውን ጸጋ ለይተው ቀልጣፋ እና የዘመኑ የአገልግሎት አሰጣጦችን ተግባራዊ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል ፡፡ የስማርት ሲቲ ጽንስ ሀሳብ አስመልክቶ የውይይት ሰነድ ያቀረቡት የመሬትና ካደስተር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ብዙዓለም አድማሱ፤ በከተሜነትና በከተማ ዕድገት ዙሪያ የዓለምን ተሞክሮ ያቀረቡት ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሰቲ መምህር ዳንኤል ሊርቦ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የከተሞች ዕድገት ተሞክሮ ከከተማ ፕላን መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘለቀ አግዋር ሰነዶች ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጓል፡፡ በቀጣይ ቀናት የተለያዩ ከተሞች ልምድና ተሞክሮዎቻቸውን አቅርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው በመርሃ-ግቡሩ ተመልክቷል፡፡፡

Posted in: ዜና